አንድ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ዲን ህጋዊ ክፊያ በማጭበርበር ለቤተሰቡ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ክፊያ እንዲፈፀም አደረገ።

በዩንቨርሲቲው የማህበረሰብና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን ረዳት ፕሮፌሰር አብራሃም ከበደ የተባሉ ግለሰብ በእናት፣ እህት፣ ወንድምና ቅርብ ዘመድ ስም በአንድ ቀን ከዩኒቨርስቲው በጀት ከአንደ ነጥብ ግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በግል አካውንታቸው እንዲገባ ማድረጉን ለWT ሚዲያ አፈትልኮ የደረሰው የሰነድ መረጃ ያመለክታል።

በማህበረሰብና ስነሰብ ኮሌጅ የተዘጋጀውን ስልጠና ክፊያ ተገን በማድረግ የረዳት ፕሮፌሰር አብራሃም እናት ወይዘሮ ሴፍነሽ ኪዳኔ ስም ሁለት መቶ ሺህ ብር፣ በወንድሙ አቶ ዘላለም ከበደ ስም ሁለት መቶ ሺህ ብር፣ በእህቱ ሜሮን ከበደ ስም ሁለት መቶ ሺህ ብር፣ በእህቱ ፀሀይነሽ ከበደ ስም ሁለት መቶ ሺህ ብር፣ የቅርብ ዘመድ እምበት ሎላሞ ስም አጠቃላይ ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ቀጥታ በንግድ ባንክ አካውንት እንዲገባ አድርጓል።

በተመሳሳይ በስልጠናው ምንም አይነት ተሳትፎ የሌለው አቶ መሰለ ማንዳዶ የዩንቨርስቲ ሰራተኛና በእሱ ቤተሰብ ግል አካውንት ስምንት መቶ ሺህ ብር እንዲገባ ማድረጉን ለWolaita Times ሚዲያ ከተላከው ስነድ ማረጋገጥ ችለናል።

በተጨማሪም በዚሁ ክፊያ ቁጥር 21 ላይ በዩንቨርሲቲው ፕረዚዳንት ስምና አካውንታቸው ላይ 200.000 ብር እንዲገባ ተደርጓል።

ባለፈው ሳምንታት የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ላይ በርካታ የኦዲት ግኝቶች መገኘቱን ተከትሎ በአስር ቀናት ውስጥ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ ተወስዶ ሪፓርት እንዲደረግ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ትዕዛዝ ቢሰጥም እስካሁን ምንም አይነት እርምጃ እንዳልተወሰደ አረጋግጠናል።

የ Wolaita Times ሚዲያ ከህዝብና ከተቋም ተጠቃሚነት ይልቅ የግል ጥቅምና ፍላጎት ለማሟላት የሚጥሩ ግለሰቦችን እንዲህ በመረጃና ተጨባጭ ስነድ በማድረስ የተባበሩ አካላትን እያመሰገነ በቀጣይም መሠል መረጃዎች እንዲያደርሱ ጥሪ ያቀርባል። Wolaita Times

1 thought on “አንድ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ዲን ህጋዊ ክፊያ በማጭበርበር ለቤተሰቡ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ክፊያ እንዲፈፀም አደረገ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: