የአማራ ክልላዊ መንግስት የሰላም ስምምነቱ በጣሰ እና በተቃደ መንገድ የትግራይ ምዕራባዊ ዞን አሰፋፈር እና ዲሞግራፊ ለመቀየር ብዛት ያላቸው መጤ ሰፋሪዎች ወደ ምዕራብ ትግራይ ማስገባቱ ተገለፀ።

በትናንትናው ዕለት የአማራ ክልላዊ መንግስት ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች ከ76 በላይ ተሽከርካሪዎች አስጭኖ ያጓጓዛቸው መጤ ሰፋሪዎች በዛሬውዕለት ወደ ትግራይ ምዕራባዊ ዞን የተለያዩ አከባቢዎች አስገብተዋቸል።

ይህ ቀደም ሲል የጀመረው የአካባቢው ዲሞግራፊ የማስለወጥ እኩይ ተግባሩ ቀጣይነት  ያለው ወረራ መሆኑን የተናገሩት ምንጮቹ በዛሬው እለት ከገቡት ከ76 በላይ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርሪዎች የተጫኑ ተሳፋሪዎች ወስጥ 50 ተሽከርካሪዎቹ በቃፍታ አከባቢ፣ ባዕኸር፣ ግይፅ እና ሩዋሳ እንዲሰፍሩ እያደረገ ሲሆን ከሃያ ስድስት በላይ ተሸከርካሪዎች የተጫኑት መጤ ሰፋሪዎች ደግሞ ወደ ፀገዴ አከባቢ፣ እምባ ጋላ እንዲሰፍሩ አድርጓል።

ከተለያዩ የአማራ ክልል የተሰባሰቡ አዳዲስ ሰፋሪዎችን ማጓጓዙን ያልካደው የአማራ ክልል መንግስት ባለስልጣናት ይህንን አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት እየተጠቆመ ነው።

የአማራ ክልል መንግስት አስቀድሞ በርካታ አዳዲስ መጤ  ሰፋሪዎች ማስገባቱ የጠቀሙት የድምፂ ወያነ  ኢንተርናሽናል ምንጮች የቆራሪት ከተማ በአዲስ በመጡት የአማራ ክልል ሰፋሪዎች የተጨናነቀች ስትሆን አብዛኛዎቹን በጦርነቱ የተፈናቃሉ የተጋሩ መኖርያ ቤቶች ሰብረው በመግባት እየሰፈሩበት መሆኑን አረጋግጧል።

በዳንሻ አከባቢም በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ከተለያየ የአማራ ክልል የመጡ አዳዲስ ሰፋሪዎች አከባቢው እንዲወሩት ተደርጓል።

በትግራይ ላይ በተካሄደው ወረራ በምዕራብ የትግራይ ህዝብ ዘር የማፅዳት ተግባር እንደተፈፀመ በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ደረጃ የተረጋገጠው የአማራ ወራሪዎች ተግባር አሁንም ያንን ተግባራቸው አጠናክረው በመቀጠል እዛ የቆየው ህዝብ በማፈናቀል እና አረመኒያዊ ተግባራት በመፈፀም ተጠምዷል።

በሰላም  ስምምነቱ መሰረት በወረራ ከያዙት የትግራይ አከባኒዎች በአስቸኳይ መውጣት የነበረባቸው እነዚህ ሃይሎች አሁንም ወረራው አጠናክረው በመቀጠል የተጀመረው ሰላም ሂደት የጣሰ ተግባራቸውን ቀጥለውበታል ስል ድምፅ ወያኔ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: