
በመብት ተሟጋችና ፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አንዱስለም ታደሰ የተፃፈ አዲስ መፃሀፍት በቅርቡ ለአንባብያን እንደሚደርስ ተገለፀ።
ክለብ ኦፍ ዘኮንዲሽንድ (የታጠረባቸው) የሚል ርዕስ ያለው መፅሐፉ በቅርቡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በግንቦት 23 ቀን 2023 በይፋ ለአንባቢያን እንደሚደርስ የመፅሐፉ ደራሲ አንዱአለም ታደሰ ተናግሯል።
መፅሀፉ በ427 ገፅ በእንግሊዝኛ የተፃፈ ሲሆን የሚታተምበት ከተማ ለንደን መሆኑንም ደራሲው አብራርቷል።
መጽሐፉ “ገና በልጅነት በኅብረተሰቡ ውስጥ ስላለው ኢፍትሃዊነት በጥያቄዎች የተሞላ ወጣት ሕይወት፣ አንድ ገና ያልዳበረ ማህበረሰብ በአንድ ግለሰብ ህይወት ላይ ያለውን ተፅእኖ፣ አንድ ግለሰብ በህብረተሰብ ውስጥ ምን አይነት ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል፣ ኢትዮጵያውያን ለምን ራሳቸውን ከጦርነት ስነ-ልቦና ነፃ ማድረግ እንደማይችሉ፣ እርስ በእርሳችን ላይ አጥር እንዴት እንደምናጥር፣ የድህነታችን መውጫው መንገድ የሚሉትን ሀሳቦች ለመተረክ የተነቀሰ ማስታወሻዬ ነው” ስልም ደራሲው ስለ መፃሀፉ ይዘት አስረድቷል።
መፃሃፉ ሲታተም በአማዞን እና በሌሎች ማሰራጫዎች ላይ ለሁሉም አንባብያን እንደሚለቀቅ የመፅሀፉ ደራሲና ፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አንዱአለም ታደሰ ለWT ሚዲያ አብራርቷል።
መጽሐፉን አስቀድመው ማዘዝ (preorder) ከፈለጉ https://pegasuspublishers.com/books/coming-soon እንደሚቻልም ተገልጿል።