ሰበር ዜና

በዎላይታ ዞን በማጭበርበር ምክንያት የተሰረዘው ህዝበ ውሳኔ በድጋሚ ሰኔ 12 እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልልን ለመመስረት በዎላይታ ዞን በድጋሚ የሚደረገው ህዝበ ውሳኔ፤ በመጪው ሰኔ 12፤ 2015 እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ለህዝበ ውሳኔው የመራጮች ምዝገባ የሚካሄደው፤ ድምጽ በሚሰጥበት ቀን እንደሆነም ቦርዱ ገልጿል።

ምርጫ ቦርድ ይህንን ያስታወቀው በዎላይታ ዞን በድጋሚ የሚካሄደውን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ፤ ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 26፤ 2015 በአዲስ አበባ ሳፋየር ሆቴል እያደረገ ባለው የባለድርሻ አካላት ውይይት ላይ ነው። በዚህ ምክክር ላይ የነባሩ ደቡብ ክልል እና የዎላይታ ዞን አመራሮች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

በዚህ ውይይት ላይ በድጋሚ ለሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ፤ ቦርዱ ያዘጋጀውን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል። በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ህዝበ ውሳኔው ከአንድ ወር ከ15 ቀናት በኋላ የሚካሄድ ሲሆን ውጤቱ ደግሞ በሰኔ 19 ይገለጻል። በዚህ ህዝበ ውሳኔ 998,00 መራጮች ይሳተፋሉ የሚል ግምቱን ያስቀመጠው ቦርዱ፤ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወነው በድምጽ መስጫው ዕለት ሰኔ 12 መሆኑን አስታውቋል።

የህዘብ ፍላጎት ያልተካተተበት ምርጫ በመሆኑ ውድቅ የሆነው በተመሳሳይ መንገድ ይሳካላቸው ይሁን ❓

በዝርዝር እንመጣበታለን👐

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *