ከህዝብ ፍላጎት በተቃራኒው እስከመቼ እንቆማለን” በሚል የዎላይታ ብልፅግና አመራሮች መካከል የተካረረ ጥርጣሬ፣ አለመግባባትና ክፍፍል መፈጠሩ ተገልጿል ።

በብልፅግና አመራሮች መካከል የተፈጠረው ጥርጣሬ፣ አለመግባባትና ክፍፍል መንስኤ ጥር 29/2015 ዓ.ም በዎላይታ ዞን ተካሂዶ በማጭበርበር የተሰረዘ ሕዝበ ውሳኔ ውጤት ተከትሎ መሆኑን ከአንድ “ስሜ አይጠቀስ” ያሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለWT ሚዲያ ገልፀዋል።

ሕገወጡን ፖለቲካ ውሳኔ ሕጋዊ ለማስመሰል የሚረባረበው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29/2015 ዓ.ም ዎላይታ ውስጥ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት “ተሰርቋል” ብሎ ውድቅ ካደረገ በኃላ በዋናነት የማጭበርበር ሰንሰለት ዘርግቶ ቀጥታ ትዕዛዝ ሲሰጡ የነበሩ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮችን በመተው በታች መዋቅሮች ያሉ አመራሮችን እየከሰሰ መሆኑ በቀጣይም ተመሳሳይ ማጭበርበር ውስጥ ከተገባ “አንዱ አንዱን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል” በሚል ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መግባታቸውንም ባለሥልጣኑ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት የቀበሌ እና የወረዳ አመራሮች በሙሉ “በዞንና በክልል አመራሮች ዘንድ አመኔታ የለንም፣ እኛ ካላጭበረበርን ሕዝቡ ጎጆን በፍጹም አይመርጥም፣ ነገም ተመሳሳይ ጥፋት ቢፈጸም አሳልፎ ሊሰጡንና ተጠያቂ ሊያደርጉን ነው፣ በምርጫው ሥራ ከምንሳተፍ መልቀቂያ እናስገባለን፣ በአመራርነት የምንቀጥልና የምርጫ ተልዕኮ የምንወስድ ከሆነም በሕዝቡ ላይ ምንም ጫና ሳናደርስና እንደ በፊቱ ሳናጭበርብር የሚመጣውን ውጤት በጸጋ እንቀበላለን” በማለት የዞን፣ የክልልና የፌዴራል የዎላይታ ተወላጆች የ”ስረቁ” ተልዕኮ አንቀበልም” የሚል አቋም መያዛቸውንም የመረጃ ምንጫችን አረጋግጠዋል።

በዚህ ምክንያት በየደረጃው ያሉት መካከለኛና ዝቅተኛ አመራርሮች ከምርጫው ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ከመሥራት ራሳቸውን ለማግለልና አልፎም ከአመራርነት ለመልቀቅ ማሰባቸው፣ ለዞን፣ ለክልልና ለፌዴራል ዎላይታ ተወላጆች አመራሮች ራስ ምታት እንደሆነባቸውም ለማወቅ ተችሏል።

“እናንተ ዞን፣ ክልልና ፌዴራል ቁጭ ብላችሁ በሚትሰጡት ተልዕኮ ሕዝባችንም ሆነ እኛም አላስፈላጊ ዋጋ አንከፍልም፣ መተባበር ሆነ ተልዕኮ የግድ የምትሰጡ ከሆነ ሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች ዎላይታ ብቻውን በራሱ ስም የሚጠራ ክልል መብት ጥያቄ ይመለስ የሚለውን ለማሳካት የሚሰጥ ተልዕኮ ካለ ስጡን” ያሉት አመራሮች ከምርጫ አስፈጻሚነት ከታገዱ ግለሰቦች ጋር ሕብረት እየፈጠሩ መሆናቸውንም ከባለሥልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምርጫ ቦርድ በዎላይታ ዞን የመጀመሪያውን ህዝበ ውሳኔ በከፍተኛ ህግ ጥሰት ምክንያት ከሰረዘ በኃላ በድጋሚ ሰኔ 12/2015 ዓ.ም ለማካሄድ ይፋ ማድረጉ ተከትሎ የዎላይታ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ባወጣው መግለጫ “በድጋሚ ቀጣይ የሚካሄድ ህዝበ ውሳኔ የዎላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚል አማራጭ ያልተካተተ ከሆነ ፓርቲያችን ለኢ-ህገመንግስታዊ ሪፈረንደም እውቅና የማይሰጥ መሆኑን ከወድሁ እናሳውቃለን” ስል መግለፁ ይታወሳል።

በተመሳሳይ መንገድ የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ “ዎላይታ ሕዝብ ዳግም ህዝበ ውሳኔ አጀንዳ ላይ በግልፅ “ዎላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት” የሚል አማራጭ እስካልቀረበ ድረስ ለህዝበ ውሳኔ ህጋዊ እውቅና እንደማንሰጥ እና ሂደቱንም ውጤቱንም እንደማንቀበል በአፅኦት አሳውቀን ወጥተናል” በሚል ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ማሳወቁም የሚታወስ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: