“ህዝበ ውሳኔ ማሳኪያ” በሚል የዎላይታ ብልፅግና አመራሮች ከሕዝቡ ገንዘብ በኃይል እየሰበሰቡ መሆናቸው ከፍተኛ ቅሬታ ፈጠረ

የብልፅግና ፖለቲካ ውሳኔ ሕጋዊ ለማስመሰል የሚረባረበው ብሔራዊ ምርድ “ዎላይታ ውስጥ ዳግም አካሂዳለሁ” ያለውን የፖለቲካ ውሳኔ ቅስቀሳ ለማካሄድ የዞኑ ብልፅግና አመራሮች ከሕዝቡ ገንዘብ በኃይል እየሰበሰቡ መሆናቸው በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ማስነሳቱን ከተለያዩ ምንጮች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

የሚሰበሰበው ገንዘብ “ከአዲስ አበባ ይመጣሉ” የተባሉ ከ5,000 የሚበልጡ የምርጫ አስፈጻሚዎች የተለመደውን ሌብነትና ማጭበርበር ተግባራቸውን እንዲደገፉ ጉቦ የሚሰጥ መሆኑን ስሜ አይጠቀስ ያለው ቅሬታ አቅራቢ ባለሃብት ገልጿል።

በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ከታች እስከ ላይ ያሉ የመንግስት መዋቅሮችን በማስተባበር የሚሰበሰበው ገንዘብ ለአስፈጻሚዎች “ላይበቃ ይችላል” የሚል ስጋት በመፈጠሩ በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ ሁሉም ባለሃብቶች ከነወለድ የሚመለስ ብድር እየተወሰደ መሆኑንም ከአንድ ታዋቂ ባለሃብት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተለይ ከአርሶ አደሩ “አባላ አባያ ሕዝብ ለማገዝ ነው”በሚል ያለምንም ሕጋዊ ደረሰኝ ብዙ ሚሊዮች ብር መሰብሰባቸውንም ወረዳ ውስጥ ያሉ አርሶ አደሮች መረጃው አድርሰውናል።

ከኢህአዴግ ዘመን ጀምሮ የሕዝብ ድምፅ በመስረቅ የተካኑ የዎላይታ ዞን ብልፅግና ነባር አመራሮች “የሕዝቡን መፃኢ ዕድል ለማጨለም በዚህ ደረጃ ወርደው መረባረባቸው እጅግ የሚያሳዝን ክፉ ተግባር” ስሉ በርካቶች አስተያየት እየሰጡ ነው።

ከሕዝብ ገንዘብ በኃይል የመሰብሰብ ሂደቱ አስከ አሁን የቀጠለ ስሆን ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ደርሶ “ሃይ” ካላለና ካለስቆመ ሠላማዊ ሕዝብ መካከል ከፍተኛ ሁከትና ብጥብጥ ሊያስነሳ እንደሚችልም ተሰግቷል።

በሌላ በኩል ምርጫው ሕጋዊ አለመሆኑንና ሕዝቡ መሳተፍ እንደማይገባ የሚያስገነዝቡ ግለሰቦችንና ቡድኖች አስረው እያሰቃዩ መሆናቸውም ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *