አምስት ሀገራዊ ፓርቲዎች ትብብር በኢትዮጵያዉያን ባለቤትነት የሚመራ ሁሉም ሀገር ወደድ በጋራ የሚሳተፍበት አስቸኳይ ሀገር አድን ዉይይት በገለልተኛ አፍሪካ ሀገር እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።

ቀድም ብለዉ ትብብር በመመስረት በጋራ ሲሰሩ ከነበሩት ኢህአፓ፣መኢአድ እና እናት ፓርቲ በመቀጠል የአማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ፓርቲ በመጨመር በአምስት ፓርቲዎች ትብብር መፍጠሩን ትናንት በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል።

በኦሮሚያ ክልል ታጥቀዉ ከሚንቀሳቀሱ የኦርሞ ነፃነት ሰራዊት እና በአማራ ክልል ከመንግስት ጋር ግብግብ የፈጠሩት መንግስት ኢ-መደበኛ ብሎ ከጠራቸዉ አካላት ጋር ግጭቱን በሰላም በመፍታት ወደ ዉይይት መምጣት ካልቻልን፣ ወደ ለየለት የእርስ በርስ ጦርነት መግባታችን አይቀሬ ነዉ ሲሉ የእናት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ሰይፈስላሴ አያሌዉ ተናግረዋል።

የትብብሩ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ በመግጫዉ እንደገለፁት ከሆነ ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ እንድ ፓርቲ ብቻዉን መፍትሄ ወደማያመጣበት ሁኔታ ላይ መገኘታንን በመገንዘብ የተደረገ ትብብር ነዉ ብለዋል።

በመግለጫዉ ከትብብሩ በተጨማሪ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን ሀገርን ማዳን የሚያስችል አስቸኳይ ዉይይት እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።

ዉይይቱ ጉዳዩ ያገባናል የሚል ማንኛዉም ወገን የሚሳተፍበት ሲሆን በአፍሪካ አገር ርዕሰ ከተማ ለሁሉም አካላት ደህንነት ሲባል የሚካሄድበት መሆን አለበት ተብሏል።

በአገር አድን ዉይይት መንግስት እንደ አንዱ ተወካይ የሚሳተፍ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ነፍጥ አንስተዉ የትጥቅ ትግል እያደረጉ ያሉ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት፣ታጣቂ የአማራ ሀይሎች እንዲሁም ተመዝግቦ ያለ የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲ፣የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች የሚሳተፉበት ነዉ ተብሏል።

የዉይይቱ ዋና ዓላማ በሀገሪቱ ያለዉን ከፍተኛ የሆነ የሰላም እጦት መፍትሄ ማፈላለግ መሆኑን የገለፁት ፕ/ሮ ዝናቡ ሀገር በበርካታ ችግሮች ተሸብባለች በተለይ መዲናዋ አዲስ አበባ በተለያዩ ታጣቂ ሀይሎች ማዕከል ሆናለች አዲስ አበባ እንደ ሞቃዲሾ ሳያደርጓት ዉይይት ምንም መፍትሄ ያሌለዉ ጉዳይ ነዉ።

ሀገር አድን ዉይይቱም ስምንት የአቋም መግለጫ የተሰጠ ሲሆን መንግስት ይህንን የሰላም ጥሪ በአንድ ወር ግዜ ዉስጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኮይ ቀን ወስኖ ምላሽ እንዲሰጥበት ትብብሩ አሳስቧል።

መንግስት ይህንን የሀገር አድን ዉይይት የማይቀበል ከሆነ በተለያዩ የሰላም ትግሎች ጫና ለመፍጠር እንዳቀደወም ትብብሩ አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: