በታዋቂው ጀርመን ዶቼቬሌ ሚዲያ 👇

በዎላይታው ሙዚየሙ ከሚገኙ የሚዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ማህበረሰቡ በወቅቱ ይገለገልበት የነበረው የመገበያያ ገንዘብ ነው፡፡ ይህ ከብረት የተሠራውና “ማርጯ“ የሚል መጠሪ ያላው የመገበያያ ገንዘብ እስከ ቀይ ባህር ድረስ ለንግድ ልውውጥ ያገለግል እንደነበር በበርካታ የውጭ አገር ተጓዦች ተፅፎ እንደሚገኝ አቶ እያሱ ጠቅሰዋል፡፡

በዎላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የዎላይታ ባህላዊ ሙዚየም ገዘፍ ያለና በባህላዊ የጎጆ ንድፍ የተገነባ ሰፊ የትዕይንት ማሳያ አለው ፡፡ ዙሪያው በአገር በቀል እጽዋቶችና ዛፎች የተሸፈነ ነው ፡፡ አቶ እያሱ ገጃቦ በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአገር በቀል ዕውቀት ጥናት ተቋም ውስጥ የባህል፣ የቅርስና የታሪክ ተመራማሪ ናቸው።

የዎላይታ ብሄር ባህላዊ የአኗኗር ዘይቤ ከመኖሪያ ጎጆው ውጪያዊ ገጽታ ይጀምራል የሚሉት አቶ እያሱ “ ዎላይታ በመኖሪያው አካባቢ የሚገኘውን ቦታ ዝም ብሎ አይተውም፡፡ እያንድንዱ ለምግብ እና ለመድሃኒትነት የሚያገለግሉ አገር በቀል እፅዋቶችንና ዛፎችን በመኖሪያ ጎጆው ዙሪያ ይተክላል፡፡ በዚህ ሙዚየምም ይህን ነባር ጠቃሚ ልማድ ለማሳየት ተሞክሯል“ ብለዋል፡፡

የዎላይታው የባህል ፣የቅርስና የታሪክ ተመራማሪው አቶ እያሱ እንደሚሉት ዎላይታ ለረጅም ጊዜ በጥንታዊ የመንግስት ሥረዓት ሲመራ ነው የቆየው፡፡ የመንግሥታዊ አስተዳደር ልማድ ከቀደሙት አባቶች የአስተዳደር ዘዬ የተቀዳ እንደነበር አቶ እያሱ ይናገራሉ፡፡ ህዝቡ በሦስት ሥርወ መንግሥታት ከካዎ ቢቶ እስከ ካዎ ጦና ድረስ በ52 በላይ ነገስታቶች ሲተዳደር እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፡፡

በወቅቱ በሥረወ መንግሥታቱ መካከል ይከናወን የነበረው የሥልጣን ቅብብሎሽ ግን መመዘኛው ሌላ ሳይሆን ነገስታቱና መንግሥታቸው ለህዝቡ ምን ሠሩ የሚለው እንደነበር አቶ እያሱ አስረድተዋል።

በዎላይታው ሙዚየሙ ከሚገኙ የሚዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ማህበረሰቡ በወቅቱ ይገለገልበት የነበረው የመገበያያ ገንዘብ ነው ፡፡ ይህ ከብረት የተሠራውና “ማርጯ“ የሚል መጠሪ ያላው የመገበያያ ገንዘብ እስከ ቀይ ባህር ድረስ ለንግድ ልውውጥ ያገለግል እንደነበር በበርካታ የውጭ አገር ተጓዦች ተፅፎ እንደሚገኝ አቶ እያሱ ጠቅሰዋል፡፡

በመዚየሙ ለእይታ ከቀረቡት ባህላዊ ቁሶች መካከል የብሄሩ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ሌላው የተመልካቹን ቀልብ የሚስቡ ናቸው፡፡ በየመልካቸው ተሰድረው የሚገኙት የሙዚቃ መሣሪያዎች ምን አይነት አገልግሎት አላቸው ለሚለው አቶ እያሱ ሲያብራሩ “ለምሳሌ ዲንኬ እና ጨቻ ዘዬ የተባሉት የትንፋሽ መሳሪያዎች ለደስታ እና ለሀዘን ያገለግላሉ፡፡

በተለይ ደግሞ ነገሪታ የተባለው የምት ከበሮ ለቤተ መንግሥት ሥራ ያገለግል ነበር፡፡ ለምሳሌ ነገሬታው ሦስት ጊዜ ከተመታ በቤተ መንግሥት ግቢ ለቅሶ መኖሩን፤ አራት ጊዜ ከተመታ ደግሞ ሹመት እንዳለ ለህዝቡ መልዕክት ይተላለፍበት ነበር “ ብለዋል፡፡

የዎላይታ ማህበረሰብ በታታሪ ሠራተኝነቱ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ዛሬ ላይ የሚገኘው ትውልድ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በወዙና በላቡ አገር ሲያቀና ማየት የተለመደም፤ የሚታይም እውነት ነው፡፡ ይህ የታታሪነት ባህል ታዲያ ታሪካዊ ዳራ አለው ይላሉ የዎላይታ፣ የቅርስና የታሪክ ተመራማሪው አቶ እያሱ፡፡

በጥንታዊ የዎላይታ ሥረዓት አንድ የማህበረሰቡ አባል በልፋቱ ሠርቶና ደክሞ በርካታ ቁጥር የላቸው ከብቶችን ማርባት ከቻለ ንጉሱ ፊት ቀርቦ ባህላዊ ማዕረግ ይሰጠው እንደነበር አቶ እያሱ ይናገራሉ።

ከዎላይታ ብሄር ነባር ባህላዊ እሴቶች መካከል የጠላት ወረራን መከላከል የማህበረሰቡ አባል ግዴታ ነው፡፡ በጦር ሜዳ ጠላትን ድል ላደረጉ ሰዎች ማህበረባዊ ዕውቅና በመስጠት ሽልማቶች እንደሚበረከቱላቸው የጠቀሱት አቶ እያሱ“፡ የጦር ጀግንነት ሽልማቶችም በውጊያው አንደሠሩት የጀብድ መጠን የተለያየ ነው፡፡ ከዝሆን ጥርስ የሚሠራ አንባር፣ ከብር የሚሠራ የጆሮ ሎቲ ወይም ባለቀለም የወፍ ላባ ሊሆን ይችላል” ብለዋል፡፡

በዎላይታ የባህል ሙዚም አሁን ላይ በየቀኑ በበርካታ ሰዎች እየተጎበኘ ይገኛል፡፡ ይህም ከተለያዩ አካባቢዎች ለሚመጡ ጎብኚዎች የብሄሩን ቀደምት አኗኗር ለማወቅ መልካም አጋጣሚ ሆኗላቸዋል፡፡ ሙዚየሙን ተመልክተው ሲወጡ አግኝተን ያነጋገርናቸው ጎብኚዎችም ያረጋገጡልን ይህንኑ ነው።

የሚጨበጥ የሚዳሰስ የህያው ታሪክ ባለቤት- ዎላይታ ህዝብ ታሪክ በዶቼቬሌ የተፃፈ
Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *