በአንድ አመት ውስጥ ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ዩንቨርስቲዎች ከአራት በላይ ማስተርስ ድግሪ ተሸላሚ በመሆን ያጠናቀቀው ኢትዮጵያዊ

እንጂነር ደሳለኝ ዳካ ይባላል፣ የዎላይታ ተወላጅ ነው፣ የመጀመሪያ ድግሪ በ1998 ዓ.ም ከአርባምንጭ ዩንቨርስቲ በስቪል እንጂኔሪንግ የሜዳልያ በመሸለም ተመርቀው ነበር፣ እንደተመረቀ ለአጭር ጊዜ በመንግሥት ኃላፊነት ላይ ሰርቷል፣ የመንግስት ኃላፊነትን በገዛ ፈቃዱ በመልቀቅ የረዥም ጊዜ ህልሙ የነበረውን ከአንድ አስርት አመታት በላይ ጀምሮ በግል ጥረቱ ለማህበረሰቡ የተለያዩ በጎ ተግባር ሥራ ላይ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።

እንጂነር ደሳለኝ የሚመራው ተቋም ከፍተኛ የግል ጥረት የሚፈልግ በመሆኑ ተጨማሪ ትምህርት ለመማር አስር አመታትን ፈጀበት።

የትምህርት ጥማቱን ለማርካትና ተጨማሪ የእውቀት ለመሸመት ከመጀመሪያው ድግሪ ትምህርት ዘርፍ ጋር በምንም የማይገናኝ ለቀጣይ ጉዞ ያግዛል ብሎ ያሰበውን ለመማር ቀድሞ የሚሰጠውን ፈተና ተፈተነው በሚገርም ሁኔታ ከተፈተኑ ዘርፉ ተማሪዎች በበለጠ በሁሉም ከፍተኛ ማለፊያ ውጤት በማስመዝገብ ቀጠለ።

አራቱንም ትምህርት በከፈትኛ ውጤትና ስኬት የጨረሰ ቢሆንም የተደራረበ ስራና የትምህርት ጊዜ ስለነበር በቦታው መገኘት አልቻለም።

በዛሬው ዕለት በሁለት ማስተርስ ድግሪ የማዕረግ ተመራቂ ቢሆንም ሁለቱን መድረስ ጊዜ ባለመኖሩ በሐዋሳ ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ በMA in International Relations and Diplomacy (3.87) ምረቃ ቦታ ሳይገኝ በዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ በአካል በመገኘት MA in Socio-Economic Development and Planning (3.97) የሜዳልያ ሽልማት በመውሰድ ተመርቋል።

በተለይም በአውሮፓ የስፔን MA in International Cooperation and Humanitarian Aid (Spain) ትምህርት በOnile እና ጥናታዊ ጽሁፍ ደግሞ በአካል የሚቀርብ ቢሆንም ካላው የስራ ጫና እንዲሁም በሀገር ውስጥ እየተማረ የነበረውን ትምህርት እንዳይስተጓጎል የተመቻለትን ጉዞ በመሰረዝ ከኢትዮጵያ ሆኖ ለማቅረብ ያቀረበው ጥያቄ በዩንቨርሲቲው ተቀባይነት አግኝቶ ጥናታዊ ፅሁፍ በማቅረብ ውጤቱም ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቦ እዚያው ዩንቨርስቲ ውስጥ የመምህርነት ዕድል የቀረበለትን አልተቀበለውም።

በሌላ በኩል አራተኛ የማስተርስ ድግሪ በExecutive Community Leadership from Addis Ababa University/Jönköping University (Sweden) ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በመመረቁ በዩንቨርሲቲው በመምህርነት እንዲሰራ የቀረበለትን ጥያቄ አለመቀበሉ ተገልጿል።

የ SHAPEthiopia በጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና ባለቤት እንጂነር ደሳለኝ ዳካ በዎላይታ ሻንቶ ከተማ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በራሱ ጥረት ከተለያዩ አለምአቀፍ ተቋማት ጋር በመፃፃፍ ያስገነባው የማህበረሰብ ቤተ-መጻሕፍት ህንፃ በጥቂቱ ለአብነት የሚጠቀስ ሲሆን ላይብሬሪው ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ለምርምር እና ጥናት አገልግሎት የሚውሉ ከ22,000 በላይ በሀገር ውስጥ የማይገኙ ውድ በዘመናዊ ኮምፒተሮች ጭምር የተጫኑ መጽሐፍትን ከተለያዩ አለማት በማስመጣት ለበርካቶች በነፃ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተነግሯል።

በአንድ አመት ውስጥ አራት የማስተርስ ድግሪ በከፍተኛ ውጤት ማግኘት የቻለው እንጂነር ደሳለኝ በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ አለምአቀፍ በጎ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በርካታ ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ተማሪዎችን ሙሉ ወጪ በመሸፈን ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩንቨርስቲ በማስተማር፣ ባሎቻቸውን በሞት ያጡ ወገኖቹን በተለያዩ መንገዶች ቋሚ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ እንዲሁም በትምህርትና በጤና ዘርፍ በዎላይታ ዞን፣ በጋሞ ዞን እንዲሁም በሲዳማ ክልል ለበርካቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ጭምር እየሰራ የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።

ከዚሁ ግለሰብ መማር ያለብን በርካታ መልካም ተሞክረው ይኖራል። ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት እዚህም እዚያም አብዛኛዎቻችን “ለኔ ብቻ ይሁንልኝ” በሚል በስግብግብነት የመንግሥትንና የህዝብን ሃብት በዝብዘው ራሳቸውን በሚገነቡበት ወቅት እንደዚህ አይነት ትውልድን የሚሻገር መልካም ተግባር የሚያከናውኑ ግለሰቦች በመንግሥት በህዝብም ዘንድ ዕውቅናና ድጋፍ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

በተላይም በዎላይታ በርካታ እምቅ የተማሩ ምሁራን የሚገኝበት በመሆኑ ሁሉም እንደ እ/ር #ደሳለኝ የበኩላቸውን ድርሻ ቢወጣ ለዎላይታ ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚተርፍ ውጤታማ ሥራ ልንሰራ እንችላለን፡፡

እርስበርስ መተቸትና የፖለቲካ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው በመተባበር የቻልነውን ያህል ጥረት በማድረግ ለማህበረሰቡ የሚበጀውን ተግባር ማከናወንን የዘወትር ተግባር ማድረግ ወቅቱ የሚፈልገው ወሳኝ ነገር መሆኑን ሁላችንም መገንዘብ አለብን፡፡

ለእንጂኔር ደሳለኝ ከእነ ቤተሰቦቹ እንኳን ደስ ያለህ እያልን ለቀጣይ ለማህበረሰቡ በራስህ ጥረት እያደረክ ያለውን በጎ ተግባር አጠናክረህ እንድምትቀጥል በመተማመን ነው👐
Wolaita Times

  1. MA in International Cooperation and Humanitarian Aid (Spain);
  2. MA in Executive Community Leadership from Addis Ababa University/Jönköping University (Sweden)
  3. MA in International Relations and Diplomacy from Hawassa University
  4. MA in Socio-Economic Development and Planning from Wolaita Sodo University;

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: