“የአማራ ፋኖ የአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕከል አርባምንጭ እንዲሆን በሚዲያው በኩል ይፋ ማድረጉ ያሳሳብናል” በዞኑ የሚገኙ ብሄረሰቦች

በጋሞ በአርባምንጭ እና አከባቢው የሚገኙ ብሄረሰቦች ማንነታቸው በሶስተኛ አካል ጠልቃ ገብነት ለበርካታ ዘመናት ታፍኗል አሁንም በቀጣይ ለማፈን እየተደረገ ያለው ጫና ታውቆ ማነንቱን የሚያከብርና የሚወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከጎናችን መሆን አለበት” ሲሉ አስረድቷል።

አስተያየት ሰጪዎቹ በዞኑ የቁጫ፣ የዘይሴ፣ የጋንታ፣ የዶርዜ፣ የቦሮዳ፣ የኦቾሎ እንዲሁም በዞኑ የሚገኙ ነባር ብሄረሰቦች ማንነታቸው እንዳይታወቅ ከፍተኛ ስቃይና አፈና እየተካሄደ መሆኑን አጋልጧል።

አሁንም ተመሳሳይ ስቃይና መከራ በእነኝህ ጭቁን ብሄረሰቦች ላይ ለማድረስ በራሳቸው ክልል ተቀምጦ በሌላ ክልል ውስጥ ጫና ለመፍጠር እያደረጉ ያሉት (ፋኖ) እቅድ ይፋ ማድረጉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሆነ መንግስት እንዲያውቅልን እንፈልጋለን ስሉ ቅሬታ አቅርቧል።

ፋኖ አንድ እግሩን በአርባምንጭ ሌላኛውን ጎንደር አድርጎ በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጫና ለመፍጠርና ድብቅ አላማ ለማሳካት ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የዘረጋውን መረብ መበጠስ በራሳቸው ማንነት ለሚኮሩ እንዲሁም የሌሎች ጭቁን ብሄረሰቦች ማንነት እንዲታወቅና መብታቸው እንዲከበር ለሚታገሉ ሁሉ እፎይታ የሚፈጥር በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ከጎናቸው ሊሰለፉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል አንድ የዎላይታ መብት ተሟጋች “እንግዲህ የገባንበት ትግል የዎላይታን ሕዝብ አርባምንጭ አምጥቼ ካልገዛሁ ከሚል ቡድን ጋር ብቻ አለመሆኑን አውቀህ ለአዲስ የትግል ስልት ራስህን አዘጋጅ” ብሏል።

“Zehabesha የተሰኘ አሮጌ ሥርዓት ናፋቂ ባለረዥም እጅ ጣልቃ ገብ ሕልመኛ ምን እየሠራ እንደሆነ ካያያዝኩት ፎቶ ማየት ትችላላችሁ። ያለሦስተኛ ወገን ድጋፍ ራሱን ችሎ ታግሎ የማያወቀው፥ የሦስተኛ ወገን ሳንባ ተውሶ መተንፈስ እየተጣጣረ ነው። ለመተንፈስ የሚያደርገው መጣጣርም ማህበራዊ ሚዲያን አጨናንቆታል” ስሉ ሁኔታውን አስረድቷል።

“የዎላይታ ሕዝብ ዕጣ ፋንታ የሚወሰነው በሕገ መንግሥት በተረጋገጠው መብት መሠረት በራሱ በዎላይታ ሕዝብ እንጂ በእናንተ በጨፍላቂ አሮጌ አስተሳሰብ አይደለም። የአማራ ሕዝብ ዕጣ ፋንታ በሕገ መንግሥት እንጂ በፌስ ቡክ በሰበሰብከው ድምፅ እንደማይወሰን ሁሉ፥ የኦሮሞም ሕዝብ ዕጣ ፋንታ በሕገ መንግሥት እንጂ በፌስ ቡክ በተሰበሰበ ድምፅ እንደማይወሰን ሁሉ፣ የዎላይታም ሕዝብ እና የሌሎቹም ሕዝቦች ዕድል የሚወሰነው በሕገ መንግሥት በተረጋገጠው መብት መሠረት በራሱ በሕዝቡ ድምፅ እንጂ በፌስ ቡክ በተሰበሰበ ድምፅ አይደለም።” በማለት አካሄዱን ኮንኗል።

“እናንተ የካዛንቺስ ልጆች ታላቁን የአማራ ሕዝብ በማይመጥን ተግባር ውስጥ አትግቡ። ይህ የተከበረውን ሕዝብ የማይመጥን ያልሰለጠነ ተግባር ነው አቁሙ። እኛ ዎላይታ ሶዶን ማዕከል ያደረገ ክልል እንጂ ባሕር ዳር ወይም ጎንደር የእኛ ከተማ ይሁን የሚል ጥያቄ በምክር ቤታችን አላነሳም።” ብሏል።

“አገርቷ በአጣብቂኝ ባለችበት በዚህ ሰዓት ሦስት ክልል የዘለለ ረዥም እጅ ዎላይታን ለመነካካት በመሞከር በመንግሥት ላይ ተጨማሪ ጫና ለማሳረፍ አስባችሁ ከሆነ አይቻላችሁም! አስፈለጊ ከሆነ እናንተ ራሳችሁ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በማሳሳት በሰራችሁት ሴራ ተገደን የገባንበትን ተቃውሞ ሁሉ አቁመን እንደ ሕዝብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ጎን በመቆም አጋርነታችንን እናረጋግጣለን።” ስልም ሀሳቡን ገልጿል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: