የ “ኃይሌ ማሪያም እና ሮማን ፋውንዴሽን” በደቡብ ኦሞ ዞን ለሁለት ወረዳዎች የአምቡላንስ እና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎችን ድጋፍ አደረገ።

በአምቡላንስ ርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ የደቡብ ኦሞ ዞን ም/አስተዳዳሪና ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደሰ ካይ የሀይሌ ማሪያም እና ሮማን ፋውንዴሽን በዞናችን በአርብቶ አደር ወረዳዎች ላይ እያደረጉ ያለዉን የልማት ተግባራትን በዞኑ ስም አመስግነው የፋውንዴሽኑን አድማስ በማስፋት በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች ላይ ድጋፉ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ተወካይ አቶ ታምራት አሰፋ በበኩላቸው የሮማን እና ሀይሌ ማሪያም ፋውንዴሽን የጤና ተቋማትን የውስጥ አቅም እና የጤና ባለሙያዎችን የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሠጡ እንደቆዩ ገልፀው በአርብቶ አደር ወረዳዎች ላይ ዳሰሳ ስደረግ በጉድለት ወይም አርብቶ አደሩ የጠየቋቸውን ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠታቸው አመስግነዋል።

የሀይሌ ማሪያም እና ሮማን ፋውንዴሽን ሥራ አስፈፃሚ የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋየ በበኩላቸው ከአለም አቀፍ ለጋሽ አካላት ጋር በተደረገው ቅንጅት በሀመር ወረዳ ዲሜካ እና ሻንቆ፣ በበና ፀማይ ወረዳ ቃቆ እና ሻላ ጤና ጣቢያዎች ላይ ጎልቶ የሚታዩ ከእናቶችና ሕፃናት አገልግሎት ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር ለመቅርፍ የአምቡላንስ እና የአልትራ ሳውንድ ድጋፍ እንዳደረጉ ገልጸዋል።

በመድረኩ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ስሜኝ ተስፋየን ጨምሮ የሀመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ፣ የበና ፀማይ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ እና ለሌች የሚመለከታቸው የጤና ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች መገኘታቸውን ከዞኑ ጤና መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *