

ኢትዮጵያዊው የዎላይታው ተወላጅ አቶ ፋሲካ ላቾሬ የዓለም አቀፉ IMCS Pax Romana ዋና ጸሃፊ ሆነው ተመረጡ።
አቶ ፋሲካ ላቾሬን ለዚሁ ለአምቀፉ ተቋም ዋና ጸሃፊ ሆነው የተመረጡት ከሳምንት በፊት (July 2-9/2023) በታይላንድ በተካሄደው የእንቅስቃሴው አለምአቀፋ ጉባኤ/World Assembly/ ላይ በተደረገው ምርጫ ላይ መሆኑንም ተቋሙ በድሬገፁ አስነብቧል።
ጉባኤውም በየአራት ዓመት የሚካሄድ የዓለም አቀፉ ጉባኤ በውድድሩ 103 ተሳታፊዎችን ከ33 የተለያዩ ሀገራት ከአውሮፓ፣ ከአፍሪካ፣ ከእስያ ከላቲን አሜሪካ እና ከሰሜን አሜሪካ የተሳተፉበት ሲሆን ይህ የካቶሊክ ተማሪዎች መሪዎችን፣ ታዛቢዎችን፣ አስተባባሪዎችን ያካተተ እንደሆነም ተገልጿል።
አቶ ፋሲካ ላቾሬ በዎላይታ ዞን አረካ ከተማ የተወለዱ ሲሆን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2018 በአይቮሪ ኮስት በተደረገው በፓን አፍርካን ጉባኤ/Pan African Assembly/ ላይ የተደረገወን ምርጫ በማሸነፍ ከ2019 እስከ 2022 የመላው አፍርካ የካቶሊክ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ዋና አስተባባሪ ሆነው ማገልገላቸውን ተቋሙ አስረድቷል።



ፋሲካ ላቾሬ የዎላይታ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ሲሆን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ድግሪ እና በሶፍትዌር ምህንድስና የሁለተኛ ድግሪ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን እንዲሁም በልማት ጥናቶች ተጨማሪ ሁለተኛ ድግሪ በኬኒያ ከሚገኘው የምስራቅ አፍርካ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ናችው፡፡
የፓን አፍሪካ አስተባባሪ ሆኖ “ማህበራዊ ፍትህን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ካለው ቁርጠኝነት እና ሌሎችን ለማገልገል ያላሰለሰ ቁርጠኝነት በማሳየቱ ሰፊ ክህሎት እና ልምድ የንቅናቄውን አላማውን ለማሳካት እንደሚረዳው ያምናል” ስልም ተቋሙ እምነት መጣሉን አትቷል።
በተጨማርም ለምስራቅ፣ ምዕራብ እና ደቡብ አፍሪካ ወጣቶችን በማብቃት አመታዊ ፕሮጄክቶችን በማቀድ፣ በማስፈጸም እና በማስተዳደር ኃላፊነቱን በመወጣት ለሀገር-ተኮር ፕሮግራሞች የገንዘብ ማሰባሰብ እንዲሁም የጽሕፈት ቤቱን ፋይናንስ እና ሠራተኞችን በማስተዳደር ላይ የተሳካ ጊዜ ማሳለፉ የቀጣይ የተሰጠውን አለምአቀፍ አስተባባርነት ላይ በተገቢው እንዲወጣ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት እምነቱን ተቋሙ መስክሮለታል።
የንቅናቄው አባል ሆኖ “ከአሥር ዓመታት በላይ በተለያዩ መድረኮች የፖሊሲ ውይይቶችን ያደረገ ሲሆን ውጤቱም ማስተባበሪያው በጋራ በመስራት በሰብአዊ መብት ተሟጋችነት እና በስትራቴጂካዊ ዘመቻዎች ልማት ላይ ለተሳተፈ የድርጅቱ የሕፃናት ጥበቃ እና ደህንነት ፖሊሲን ማዘጋጀት ላይ የተካነው ልምድና እውቀት ለቀጣይ ጉዞ አቅም እንደሚፈጥርም ተገልጿል።
በኬኒያ ኖይሮቢ የአፍሪካ አስተባባሪ በመሆን ያገለገሉት አቶ ፋሲካ ላቾሬ በቀጣይ የዓለም አቀፉ ዋና ጽህፈት ቤት ወደሚገኝቤት ፈረንሳይ ፓሪስ እንደሚያቀኑም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ አቶ ፋሲካ ላቾሬ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ናቸው፡፡
ፋሲካ ላቾሬ ከዚህ የአለምአቀፉ ልምድና አበርክተው በተጨማሪ ከአለምአቀፉ ዲያስፖራ የዎላይታ ተወላጆች ማህበር ላይ የምስራቅ አፍሪካ አስተባባሪ በመሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኝ ስለመሆኑም ከግል ማህደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። Wolaita Times