ከንጉስ ስራዓት ጀምሮ እስከ ብልፅግና መንግስት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መስራቾች እና መሪዎች ለምን የዎላይታ ተወላጆች ብቻ ሆኑ ❓

የብሔራዊ ባንክ እና የህንጻው ድራፍት ዲዛይን ከዎላይታ ህዝብ ባህላዊ ቤት ጋር ምን አገናኘው⁉️

ዎላይታነት ኢትዮጵያዊነትን ይገልጻል በማለት የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥና መስራች የነበሩት ዶ/ር ምናሴ ለማ የመጀመሪያው የባንክ ህንጻ ድራፍት ዲዛይን ሰሰራ የሰጡት Concept design ጸድቆ ሃሳብ ተጨምሮ ጎልቶ እንድሰራ ታሪካዊ አሻራ ጥለዋል።

የዎላይታ ህዝብ በኢትዮጵያ ባንክ ጉልህ አሻራ የጣለና ለባንኩ ህንጻ ከፊትለፍት የጎጆ ቅርጽ እንድይዝ ያደረገና ለባንኩ መመሰረት የአንባሳውን ድርሻ የተወጣ በኢትዮጵያ ከመጀመሪያው ከንጉሱ ግዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ በመሆን ሃገርን ያገለገለ ኢኮኖሚስት ማህበረሰብ…#ዎላይታ!!

ለአንድ አገር እጅግ ታማኝና በንጽህናቸውና በዘርፉ እውቀት የተመሰከረላቸው ዜጎች ከሚፈለግባቸው ተቋማት አንዱ የገንዘብ ተቋም ነው። የአገሪቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሥርዓትን በአስተማማኝ ሁኔታ ቀጥ አድርጎ ለማቆም ብሔራዊ ባንክ ወሳኝ ነው ። ዎላይታ ካፈራቻቸው በብቃታቸው የተመሰከረላቸው ዜጎች መካከል በሶስት መንግሰታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የነበሩ የትውልድ አራያወችን እነሆ ።

           1.  የተከበሩ ዶ/ር ምናሴ ለማ

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ
————————————————–
በአጸ ሐይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያችንን በዲኘሎማትነት ያገለገሉ በፈረንሳይና በግብፅ አምባሳደር የነበሩ እንዲሁም የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ በመሆን ያገለገሉ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ኢኮኖሚት ነበሩ። ዶ/ር ምናሴ ከሰራቸው ሥራዎች አንዱ የመጀመሪው የኢትዮጵያ ባንክ ህንጻ የዎላይታ ባህላዊ ቤት (Concept drawing) በመስጠትና የባንኩን የመመሰረቻ ሰነድ ያዘጋጁ ዛሬ ላይ የቀድሞ ህንጻውን ጨምሮ በየክፍለ ሃገሩ ለሚሰራው ህንጻ አውደ ጥናት ላይ ዎላይታነት ኢትዮጵያዊነትን ይገልጻል በማለት የሰጠው Concept design ጸድቆ ሃሳብ ተጨምሮ ጎልቶ እንድሰራ ታሪካዊ አሻራ የጣለ ጀግና ነው።

      2. የተከሩ አቶ ለገሰ ሞታ

በደረግ ዘመነ መንግሰት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ በመሆን ያገለገሉ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ የባንክ አሰራር መሠረት የጣሉ ስሆን የደቡብ ምዕራብ ምዕራብ የመጀመሪያው ድስትርክት ሥራ አስክያጅ ሆኖ ስያገለግሉ ቆይተው በራሽያ ሃገር በቀሰሙት ትምህርት ፖለቲካንና ኢኮኖሚውን በማቻቻል ብሔራዊ ባንክ ገዥ በመሆን አገልግለዋል።

ከሶቭየት ህብረት ጋር በመናበብ ገንዘብ የማተምና የማሠራጨት፣ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ማስተዳደር፣ የገንዘብ ፖሊሲ የማውጣትና የመተግበር ኃላፊነት በመውሰድ ስሰራ ቆይተው በ1985 ዓ/ም የጦርነቱ መሰናበቻ እና ህገ መንግስት ማሻሻያ ስደረግ የኢትዮጵያንና የኤርትራን አካፍልና የኛንም ድርሻ ጨምረ ለኤርተራ ገንዘቡን በአስቸኳይ አስተላልፍ የሚል መልዕክት ስተላለፍ እኔ እያለው ሃገረ ተካፍላ ማየት አልፈልግም የእናት ሃገር ገንዘብ ለሻዕቢያ አልሰጥም በማለቱ የመግደል ሙከራ ሲደረግበት ሃገር ለቆ ወደ አሜሪካ ገብተዋል።

በስተመጨረሽ ለብዙ ዘመናት Bank of America ላይ የቦርድ አባልና የባንኩ አማካሪ በመሆን ስያገለግሉ ቆይተው ጡረታ ወተው በክብር በአሜሪካ ሃገር እየኖሩ ይገኛሉ።

      3. የተከበሩ አቶ ተክለወለድ አጥናፉ 

ላለፉት 23 አመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የነበሩ፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት የቀመሩ፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ዕድገት ባለቤት፤ የካምብሪጅ ዪኒቨርስቲ  ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚኪስ ተማሪ የነበሩና በአፍሪካ አህጉረ ብቻ ሳይሆን በዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን ለማሳለጥ እውቀት እና ክህሎት  አስታውጾ ከሚያደርጉት ዉሰን ሰዎች ወስጥ አንዱ የሆነው የምጥቁ አእምሮ ባለቤት ምረጥ የኢትዮጵያ ልጅ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ናቸው።

በአሁኑ ሰዓት በሚንስትር ማዕርግ የጠቅላይ ሚነስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፋይናንሰ አማከሪ ናቸው።

በአሁኑ ወቅትም የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሶሎሞን ደስታ የዎላይታ ተወላጅ ናቸው:: አሁንም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንቶች አንዱ የዎላይታ ተወላጅ እንዲሁም በተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ አያሌ  ዎላይታዎች በተለያየ ደረጃ ሀገራቸውን በታማኝነት እያገለገሉ ይገኛሉ። ይህ ዎላይታ ለኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ካበረከተውና እያበረከተ ካለው በጎ አስተዋጽኦ በጥቂቱ የተገለፀ ነው።
Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: