

አርባምንጭ ከተማ “የአዲሱ ክልል አስተዳደርና የፓለቲካ ማዕከል እንዲትሆን ትደግፋላችሁ” በሚል በከተማዋ የመሬት ስጦታ ከወሰዱ ግለሰቦች ካርታ መነጠቁ ተገለፀ።
ነባሩ ክልል ለሁለት መከፈሉን ተከትሎ እየተመሰረተ ለሚገኘው “ደቡብ ኢትዮጵያ” የተሰኘው ክልል የፓለቲካ እና አስተዳደር ማዕከል በአርባምንጭ ከተማ ላይ እንዲሆን የተለያዩ ጥቅማጥቅም መረብ ተዘርግቶ በምስጢር ሲሰራ እንደነበር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
አላማቸውን ለማሳካት ከከፍተኛ አመራሮች ጀምሮ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለተባሉ ግለሰቦች የተለያዩ መደለያ ለመስጠት ቃል የተገባላቸው ቢሆንም ነገሩ ሳይሳካ ስቀር በተለይም የመሬት ስጦታ መቅረቱን አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያለው አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።
የመረጃ ምንጩ ከአርባምንጭ ከተማ ማዘጋጃ መዝገብ ቤት ጭምር ያወጣውን ሰነድ አስደግፎ ባደረሰን መረጃ ለተለያዩ የፈደራል፣ የክልል፣ የዞንና ልዩ ወረዳዎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ለተባሉ ግለሰቦች የመኖሪያና የኢንቨስትመንት መሬቶችን በነፃ ህጋዊ አሰራር አስመስሎ በነፃ ስጦታ መሰጠቱን አረጋግጠዋል።
በተቃራኒው ሰሞኑን አዲሱ “ደቡብ ኢትዮጵያ” የተሰኘው ክልል የፓለቲካ እና አስተዳደር ማዕከል በአርባምንጭ ከተማ ላይ ሳይሆን በወጣው መስፈርት የተሻለ አፈፃፀም ላለው በዎላይታ ሶዶ እንዲሆን መንግስት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የመሬት ስጦታ ካርታ በከተማዋ ማዘጋጃ በኩል እንዲቀማና ከመዝገብ ቤት ጭምር ፍይል እንዲጠፋ መደረጉን ታማኝ የመረጃ ምንጫችን አክለው አስረድተዋል።
ከመሬት ስጦታ ባሻገር የጋሞ አመራሮች አርባምንጭ ከተማ የአዲሱ ክልል አስተዳደርና ፓለቲካ ማዕከል እንዲትሆን በርካታ ሚሊዮን ገንዘብ አውጥቶ ለተለያዩ አመራሮችና ታዋቂ ግለሰቦች መደለያ መስጠታቸውን በመግለፅ መንግስት በገለልተኝነት ያደረገው እውነተኛ ውሳኔ እንዳስደሰተውም ተናግረዋል።
በተጨማሪም የጋሞ አመራሮች “ማዕከሉ እኛ ጋር እንዲሆን ትደግፋላችሁ” በሚል የመሬት ስጦታ ከሰጣቸው አመራሮችና ግለሰቦች ከመንጠቅ ባሻገር ሰሞኑን በአከባቢው ፅንፈኛ ቡድኖችን በማደራጀት በይፋ በዞኑ በተለያዩ አከባቢዎች የዎላይታ ብሄር ማንነት በአደባባይ እንዲዘልፉ ማድረጋቸው ይታወሳል። Wolaita Times