ከክርስቶስ ልደት በፊት በዎላይታ ዞን በባይራ ኮይሻ ወረዳ የሚገኝ ሰው ሰራሽ ታሪካዊ አሩጂያ ዋሻ 👇

ይህ ሰው ሰራሽ አሩጂያ ዋሻ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ በ30 ኪ ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ስፍራን ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መሲህብ ቦታዎች እንዳሉት ይታወቃል።

በዋናነትሰው ሰራሽ የመስዕብ ቦታዎች በተለያየ ጊዜ ለተለያየ አላማ ተብሎ የተሰሩ ስሆኑ በወቅቱ ለታለመለት አላማ ከዋሉ በኃላ ለቀጣይ ትውልድ የታሪክ ቦታና ቅርስ ከመሆኑም አልፎ በወቅቱ የነበሩ የአባቶቻችን ጥበብና ለአላማ ያላቸውን ፅናት የሚያሳይ ሆኖ ለዘመናት ይቆያል።

ከዚህም አልፎ ለአካባቢው የገቢ ምንጭ ሆኖ ሲያገለግሉም እናያለን።

ከእነዚህ ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስዕብ ቦታዎች አንዱ የሆነውና በባይራ ኮይሻ ወረዳ በሴሬ ባላካ ቀበሌ ፑላሳ አምባ ላይ የሚገኘውን አንድ ታሪካዊ ዋሻ እናስተዋውቃለን።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ በሴሬ ባላካ ቀበሌ በፑላሳ አምባ መንደር ከባህር ወለል በ2,302 ሜትር ከፍታ ስፍራ ላይ የሚገኘው ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስዕብ ቦታ የሆነው የአሩጂያ ዋሻ ታሪካዊ ቦታ ነው።

ይህ ዋሻ ከክርስቶስ ልደት በፊት የተቆፈረ እንደሆነና ዋሻው የተሰራበት የአሰራር ጥበብና በውስጡ ያሉ ክፍሎች እጅግ በጣም የሚደንቅ ናቸው።

በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ልጆቻቸውንና ከብቶቻቸውን ከጠላት ለመጠበቅ፣ በጦርነት ድልን ለማግኘትና ለአደን ምቹ ቦታዎችን ለማግኘት በሚል ዓላማ የተሰራ እንደሆነ የታሪክ አዋቅዎች ይናገራሉ።

በአሩጂያ ንጉሰ ነገስታት ዘመን የነበሩ አባቶች ድንጋይን ከድንጋይ ጋር በማጋጨት እሳት አውጥቶ የተለያዩ የዱር እንስሳትን ቀንድ በመጠቀም የቆፈሩት ይህ አሩጂያ ዋሻ እጅግ ማራኪና በርካታ ታሪኮችን ጠቅልሎ የያዘ እንደሆነ ይነገራል።

ይህ የአሩጂያ ዋሻ ሶስት መግቢያ በር ያሉት ስሆን በመሃል ያለው ትንሹ እንደ መስኮት እንደሚያገለግልና አንዳንደ ጠላትን አስቀድሞ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ውሻ እንደ ሚታሰር አባቶች ይናገራሉ።

ወደ ውስጥ ስንገባ ከ300 ሰው በላይ መያዝ የሚችል ሰፊ ሳሎን ያለው ስሆን በሁሉም አቅጣጫ የተለያዩ ክፍሎች አሉት። በጣም የሚገርመው በዚህ ዋሻ ውስጥ ከ30-40 ደቂቃ መንገድ መጓዝ የሚያስችል ሁለት መግቢያዎች ያሉት ስሆን፣

የመጀሪያው ወደ አፋ ወረዳ ጎጮ ዋሻ ወደ ሚባልበት ስፍራ የሚወስድ እንደሆነና ሌላኛው ደግሞ አሁንም ወደ አፋ ወረዳ ዋዩ ዋሻ እንደሚያስወጣ የታሪክ አዋቅ አባቶች ይናገራሉ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ የሚገኘውን የአሩጂያ ሰው ሰራሽ ዋሻ እስከ ቦታው ድረስ በመሄድ እንድትጎበኙና በታሪካዊ አሰራር እንዲትደነቁ ተጋብዛቿል በማለት የባይራ ኮይሻ ወረዳ ማህበራዊ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ዘግቧል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: