ዎላሞ” የሚል መጠሪያ ታሪካዊ አመጣጥ – ከተዳፈነው ዎላይታ ታሪክ በጥቂቱ👇

ከሶስት ቀን በፊት በዛሬዉ ጋሞ ዞን በተለይም በደጋማዉ እና በአባያ ሐይቅ እና ሐማሳ ወንዞች አከባቢ ለሚኖሩ በርካታ የተለያዩ ማንነቶች፣ ቋንቋ፣ ባህልና ታሪክ ለነበራቸዉ ሕዝቦች (ቁጫ፣ ቦሮዳ፣ ጋንታ፣ ዶርዜ፣ ዘይሴ፣ ካምባ፣ ቦንኬ፣ ኦቾሎ) በአጠቃላይ “ገሙ” የሚል offensive ስያሜ የተሰጣቸዉ መሆኑን፣ ከ1974ቱ የኢትዮጵያ አብዮት በኋላ ገሙ በሚል መጠሪያ ምትክ Gaamo (Lion) የሚል synthetic የፖለቲካ መጠሪያ ስራ ላይ መዋሉን የፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም አካዳሚክ ጆርናል ዋቢ በማድረግ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ማቅረቡ ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ በዋነኝነት ዎላሞ የሚል መጠሪያ ታሪካዊ ምንጭ የተለያዩ ታዋቂ አለምአቀፍ ዌብሳይት የሰፈሩ ምርምሮችና መፅሐፍትን ዋቢ በማድረግ በአጭሩ ለማብራራት እንሞክራለን።

የዎላይታ ሕዝብ ከጥንት ዘመን ጀምሮ ራሱንና፣ አገሩን ዎላይታ ብሎ ይጠራል። ዎላይታ ዋላሄታ (ተደባለቅ/ድብልቅ ከሚል ዎላይታቶ ቃል የመነጨ concept ነዉ ተብሎ በተለምዶ ይነገራል።

በዚህ ተለምዶአዊ እሳቤ መሠረት ዎላይታ ማለት የተደባለቀ ሕዝብ እና ከተለያዩ አከባቢዎች ፈልሰዉ የመጡ ሕዝቦች ተደባልቀዉ የሚኖሩበት (an ethnic melting pot) አገር ነዉ ተብሎ በተለምዶ ይነገራል።

ይሁን እንጂ ይህ ተለምዶአዊ እሳቤ ዎላይታ እና ዋላሄታ በሚሉ ቃላት መካከል ያለዉን ድምጻዊ/phonetic ቅርርብ መነሻ የተመሠረተ reductionist view ከመሆኑም በላይ በተጨባጭ አካዳሚክ ማስረጃዎች የተደገፈ አይደለም።

ይልቁንስ ዎላይታ/ዎላይቶ ማላ እና ዶጋላ ተብለዉ በሁለት የሚከፈሉ የዎላይታ ጎሳዎች ዎላይቶ ተብሎ የሚጠራ የመጀመሪያ አባት (common ancestor ) የነበራቸዉ መሆኑን ባሊስኪ የተባለ አዉሮጳዊ ተመራማሪ በመጽሐፉ ገልጿል።

በጥንት ዘመን ዎላይቶ ከወላጆቹና ስድስት ወንድሞቹ ጋር በአሁኑ ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ዉስጥ በሚገኝ ዋሄ ጎንጎሏዋ (Wahe Rock shelter ይኖር ነበር። ከጊዜ በኋላ በዎላይቶና በስድስት ወንድሞቹ መካከል በተከሰተዉ አለመግባባት የተነሳ ወንድሞቹ ዎላይቶን ከነወላጆቹ ጋር ትተዉ ወደተለያዩ አከባቢዎች ፈልሰዉ ሄዱ።

Meanwhile ዎላይቶ ከኦሞ ወንዝ በስተሰሜን እና ምዕራብ አከባቢዎችን በራሱ ስም ዎላይታ ብሎ ጠራ። የዎላይቶ ነገድ እየሰፋ ሲመጣ ራሱን (ማንነቱን) አገሩን ዎላይቶ/ዎላይታ ብሎ መጥራት ጀመረ። እስከ ዛሬ ድረስም ዎላይታ የሕዝቡ (ማላና ዶጋላ) እና የሀገሩ/የሀገረ መንግስቱ [የጋራ መጠሪያ ሆኖ ያገለግላል።

ይሁን እንጂ ዉጫዊያን የዎላይታን ሕዝብ ሲዳማ፣ ዳሞት እና ዎላሞ ብለዉ ሲጠሩ እንደነበር ይታወቃል። ይሁንኔ ዎላይታን ሲዳማ እና ዳሞት ብለዉ መጥራት ምንጩንና ታሪካዊ መሠረቱን ማብራራት የዚች ጽሑፍ ዓላማ አይደለም።

በዚች ጽሑፍ ዎላሞ የሚል መጠሪያ ታሪካዊ መሠረት በተመለከተ በጣም አጭር ማብራሪያ ለመስጠት እንሞክራለን። እስከ 1974ቱ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮት ድረስ የዎላይታን ሕዝብ እና አገሩን ወላሞ ብለዉ መጥቀስ የተለመደ ነበር። በእርግጥ በአንዳንድ የታሪክ እና traveller ድርሳናት ዎላይታ ወይም ዎላሞ አልፎ አልፎም ሁለቱንም እያፈራረቁ ተጠቅመዋል።

በሌላ በኩል የአቢሲኒያ /የሸዋ ኦርቶ-ኣምሃራ መንግስታት የዎላይታን ሕዝብ እና አገራቸዉን consistently ዎላሞ ብለዉ ይጠሩ ነበር።

የአቢሲኒያ -ሸዋ ኦርቶ-ኣምሃራ ኤትኖክራትስ ዎላሞ የሚለዉን ቃል ይጠቀሙ የነበሩት የዎላይታ ሕዝብ offend & negatively stereotype ለማድረግ ብሎም ኤትኒካሊ ፈርጀዉ ለመጨቆን፣ ለመበዝበዝ እና structurally discriminate ለማድረግ ነበር።

ታዲያ ዎላሞ የሚል መጠሪያ ታሪካዊ ምንጩ ምንድነው ❓

ዎላሞ የሚል offensive መጠሪያ ለወላይታ(ሕዝብና አገር) የሰጠዉ ዳግማዊ ምኒሊክ ነበር የሚል ተለምዶአዊ እሳቤ አለ። According to this conventional view በዳግማዊ ምኒሊክ ጠቅላይ ጦር አዛዥነት ዎላይታን ለመዉረር የዘመተዉን፣ የአዉሮጳ ስሪት የጦር መሣሪያዎችን [በዘመኑ ዘመናዊ የሆነ] እስከ አፍንጫዉ ድረስ የታጠቀዉን ግዙፍ የአቢሲኒያ -ሸዋ ኦርቶ -ማራ ጦር traditional weapons [ጦር፣ ጋሻ፣ ጎራዴ ] የታጠቀዉ ጀግናው የዎላይታ ሕዝብ [ፈረሰኛዉና እግረኛዉ] በታላቅ ወኔ መክቶ ለመመለስ የመከላከል ዉጊያ ማድረግ ጀመረ።

ዎላይታን በአራቱም አቅጣጫዎች በመክበብ መብረቃዊ ጥቃት ይፈጽም የነበረዉ ወራሪዉ ጦር ጠመንጃ ለሚተፋዉ እሳት ከቁብ ባለመቁጠር የዎላይታ ጦር በእግርና በፈረስ እየሆነ በወራሪዉ የጠላት ጦር ላይ መልሶ ማጥቃት ያደርግ ነበር።

የዎላይታዎችን courageous and passionate መልሶ የማጥቃት እንቅስቃሴ ተገርሞ ምኒሊክ ፣ “ወይ ላሞች! ጦርና ጋሻ ይዛችሁ ጠመንጃ ለመግጠም ትገሰግሳላችሁ?” አለ። ቀስ በቀስ “ወይ ላሞች” ዎላሞ ለሚለዉ መጠሪያ አስገኘ።

በዚህ ተለምዶአዊ እሳቤ መሠረት ዎላሞ የሚል መጠሪያ after adverse incorporation/ after 1894 የመጣ ነዉ።

ይሁን እንጂ ይህ እሳቤ ትክክለኛ አለመሆኑን የሚያመላክቱ ጥቂት ማስረጃዎች አሉን።

ለምሳሌ በሸዋ ይኖር የነበረ አንድ ሚሲዮናዊ Major Harris (1840) “ከካምባታ በስተደቡብ ከሚገኘዉ ዎላሞ ከሚባል አገር የመጣ ግለሰብ ስለ አገሩ ጥቂት መረጃዎችን ሰጥቷል።

ዎላሞ small independent state ነበር። ዋና ከተማዉ ዎቶና [ ኦቶና] ይባላል። ከዚህ ቀደም ስሙ ሲጠራ የሰማሁት ኡማ ተብሎ የሚጠራ ወንዝም በአገሩ[ወላሞ/ዎላይታ ይፈሳል።

በተጨማሪም Dr Beck, on his Ethiopian language study (1845] ወላሞ ወይም ወላይታ ብሎ ጠቅሷል። ዶ/ር ቤክ በዚህ አርቲክሉ “የኔን ዎላይታ አንዳንድ ከኦሮሞ ጎሳዎች መካከል አንዱ ዎላሞ ብለዉ ይጠሯቸዋል።” በማለት ለመጠሪያ ስሙ ታሪካዊ ምንጭ ፍንጭ ይሰጠናል።

በተጨማሪም M.Antoine d’Abaddie የሚባል የአይርላንድ ተወላጅ የነበረ ምሁር የታላቁ አገረ ዳሞት ቋንቋዎች vocabularies ለጥናት ሰብስቦ የተነተነ ሲሆን የጥናቱን ዉጤት April 1845 አሳትሟል። በዚህ መጣጥፉ ዎላሞ ወይም ዎላይታ ብሎ ጠቅሷል።

በአጭሩ በ19ኛዉ ክፍለዘመን አጋማሽ [የዳግማዊ ምኒሊክ ጦር ዎላይታን adversely incorporate ከማድረጉ 50 ዓመታት በፊት] አንዳንድ አካላት ዎላይታን ዎላሞ/ዎላይታ ብለዉ ይጠሩ እንደነበር ተገንዝበናል።

ይሁንና በወቅቱ ሕዝቡንና አገራቸዉን “ዎላሞ” ብሎ መግለጹ ምንም ዓይነት pejorative /offensive connotation አልነበረዉም። ልክ የዎላይታ ሕዝብ የሐዲያን ሕዝብና አገር ማራቆ ብሎ እንደሚጠራዉ ማለት ነዉ።

ዋቢዎች 👇

👉The Journal of C.W.Isenberg and J.L. Brapf(1830;1840;1841) The Church Missionary Socuety.
👉Charles T.Beck(1845) On the Languages and Dialects of Abyssinia and the Countries to the South.
👉M.Harris(1850) “Reply to a Critique in the Bulletin of the Geographical Distribution of the Languages of Abyssinia and the Neighboring Countries(Misc.1)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *