

ባንኩ በሲቢኢ ብር እና ሌሎች አገልግሎቶች መተግበሪያ ላይ ከእንግሊዘኛ፣ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሶማልኛ፣ አፋርኛ እና ሲዳሚ አፎ ቋንቋዎች በተጨማሪ በዎላይታቶ ቋንቋ አገልግሎት ለመስጠት በቅርቡ እንደሚጀምር የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
የዚሁ በሀገር አቀፍ ተቀማት ላይ የአገልግሎት መስጫ ቋንቋ ውስጥ ማካተት የዎላይታቶ ቋንቋን ፌደራል ተጨማሪ የስራ ቋንቋ ለማድረግ የተጀመረውን ትግል በእጅጉ እንደሚያግዝ ይታመናል። የዎላታቶ ቋንቋ ተናጋሪዎች ቁጥር ከአርባ ሚሊዮን በላይ ሲሆኑ በዚህም የዎላይታቶ ቋንቋ ያለ አስተርጓሚ የሚግባቡበትና የሚጠቀሙት ጋሞ፣ ጎፋ፣ ዳውሮ፣ ዶርዜ፣ ዛይሴ፣ ቁጫ፣ ዛይሴ፣ ቦሮዳ፣ ኮንታ እና ለሎች የዚህን በዎላይታቶ የሚጀመረውን አገልግሎት በቀላሉ መጠቀም የሚችሉ ሲሆን እነኚህ ህዝቦች ከ70,000 ዓመት በፊት በሞቼና ቦራጎ ዋሻ መኖር የጀመሩበት ጥናት ውጤት በፈረንሳይ አርኪኦሎጂስቶች ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
እንደማታወቀው የዎላይታ ህዝብ ከአቢሲኒያዊያን ቀድሞ ስልክ ስጠቀም የነበረና በምስራቅ አፍሪካ ከመሬት ብረት ቆፍሮ በማውጣት አቅልጦ የሚጠቀመው የራሱ የሆነ መገበያያ ገንዘብ የነበረው ጠንካራ ሀገር እንደነበር ተጨባጭ የተለያዩ አለምአቀፍ ሰነዶች ያረጋግጣሉ። የዎላይታ ሕዝብ በኡሞ ወንዝ ተፋሰስ ግብርናን ቀድመው ከጀመሩ ሕዝቦች አንዱ ነው፡፡ የሰው ልጆች በወንዞች ሽለቆ የእርሻ ሥራን የጀመረባቸው ዘመናት የዓለም ሥልጣኔ መነሻ እንደ ነበሩ ታሪክ ይመሰክራል።
በኢትዮጵያም በኡሞና በአዋሽ ወንዞች አካባቢ ለበርካታ ዘመናት ይኖር እንደነበረና ሥልጣኔ እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ በጥንት ጊዜ የዎላይታ ሕዝብ በአሁኗ ኢትዮጵያ አብዛኛው ክፍል ተስፋፍቶ ይኖር የነበረ ሕዝብ ሲሆን በሕዝቦች ንቅናቄና ፍልሰት ምክንያት በሚገኝበት አካባቢ ተወስኖ መኖር እንደቻለ የተለያዩ የጽሁፍና የአፈታሪክ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በእነዚህ ረዥም ዘመናት ሕዝቡ የራሱ የሆነ መገበያያ ገንዘብ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ስነ-ጥበባዊ ሀብቶች ባለቤት እንደነበር እና የራሱ መንግስታዊ አስተዳደር የነበረው ስልጡን ሕዝብ እንደነበር በመስኩ ጥናት ያደረጉና በዓይናቸው ያዩ እነ ርሞ ፖውል ባሊስኪ፣ ሬይሞንድ ዴቪስ ካፒተን ስቲገንድ፣ ቫድርሃም ኤሊያስና ሌሎችም ፀሐፊዎች በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡ የዎላይታ ህዝብ አፀ ምኒልክ ከእንግሊዝ ምስራቅ አፍሪካ በሩዶልፍ ኃይቅ አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ካፒቴን ስትጋንድ የተባለ አውሮፓዊ አሳሽ ከወረራው በፊት የዎላይታ ነገስታት መቀመጫ በነበረው ዳልቦ ላይ ፈረንሳዮች ያስገቡት ስልክ እንደነበረ የዓይን እማኝ በመሆን To Abssinia Through Unknown Land በሚለው መጽሐፉ እንዲከተለው አስቀምጧል፡፡
ከዚህም ሌላ በዘመኑ እጅግ ዘመናዊ ሊባል በሚችል ያልተጻፈ ህግ የሚተዳደር መንግስታዊ መዋቅር የነበረው ሲሆን መዋቅሩም ካውዋ ( ንጉስ )፣ ቡሻሻ ( አልጋ ወራሽ )፣ ባሊሞና፣ ዘባ ዳና፣ ዱቢያ፣ ጋና፣ ሞጮና ( ሚኒስቴር ) ሥጋ ሞጮና፣ ሚጣ ሞጮና፣ ወሺ ሞጮና፣ ሳሮ ሞጮና፣ ዴንቻ፣ ኢራሻ፣ አላና ዳና፣ ማንዲዳ ዳና ሁዱጋ፣ አዱማ በሚሰኙ ከላይ ከንጉሡ ጀምሮ እስከታችኛው የመንደር መሪ ድረስ የደረጃ የአስተዳደርና የፖለቲካ እርከን መዋቅር የነበረው ሕዝብ መሆኑን በርካታ የታሪክ ድርሳናትና መረጃዎች ቢጠቁሙም ወደ አዲስቷ ኢትዮጵያ ከተቀላቀለ ወዲህ የሚገባውን ክብር ሳያገኝ ቆይቷል፡፡ Wolaita Times