ቅዱስ ወይም እርኩስ የሚባል ዘመን መለወጫ የለም !!!

በየአከባቢው የሚከወኑ በዓላት አከባበር ሁኔቶች በአስተማሪና ጥሩ ባህል ወይም በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ሊከወኑ ይችላሉ።

አዲስ ብለን የሚንቀበለው ዘመን መለወጫ እንደጊዜና ቦታው ልለያይ ይችላል እንጂ አንዱ እርኩስ ሌላውን ቅዱስ ማድረግ አይቻልም።

በየትኛውም ዓለማት ክፍል ለሚኖሩ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ባህል፣ ወግ፣ ቋንቋ፣ የአኗኗር ዘይቤ፣ የአለባበስና አመጋገብ ባህል አላቸው።

በርግጥ ከእስራኤል ሀገር ወጪ ክርስትና ወይም እስልምና ሃይማኖት ከመምጣቱ በፊት ይኖር የነበሩ ማህበረሰብ ክፍል የራሱ እምነትና አምልኮ ሥርዓት የነበራቸው ከመሆኑ አንጻር ባዕድ አምልኮ ተለማምዶ ቢኖሩም በወቅቱ ያመልኩ ለነበሩት አማልክት “በሠላም ስላደረሰ” ተብሎ የተለያዩ ዓይነት መስዋዕት ያቀረቡ እንደነበሩ ከተለያዩ ታሪክ ምንጮች መረዳት ይቻላል።

በአፍርካ ውስጥ በተለያዩ ሀገራት የራሱ የሆነ ባህል፣ ወግ፣ ቋንቋ እንዲሁም ማንነት ያላቸው ሕዝቦች የሚኖሩ ስሆን በተለያዩ ወቅት በምዕራባዊያን ቅኝ ግዛት ሥር ከተዳደሩ በኋላ ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውንና የአኗኗር ዘይቢያቸው በተጽዕኖ ሥር በመውደቁ ነባሩ ማንነታቸውን በመርሳት የምዕራባውያን ባህል መቀበላቸው በእርግጥም የታሪክ ተወቃሽ ከማድረጋቸው አላገዳቸውም።

በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ አገር በቀል ቅኝት ገዥዎች የባህል፣ የቋንቋና የማንነት ላይ ያደረሰው ተጽዕኖ በየአካባቢው ያለውን ቱባ ባህል፣ ወግ፣ ለቋንቋና ቅርስ ከትውልድ ወደ በአገባቡ እንዳይተላለፍ ማነቆ እየሆነ ይገኛል።

ለምሳሌ በእንቁጣጣሽ (በመስከረም 1) ደግሶ የበላ በዓሉን በደስታ የተቀበለ ሰው፣ በጊፋታ፣ በእሬቻ፣ በጫምባላላና በሌሎች ብሔሮች ዘንድ የሚከበረውን ዘመን መለወጫ እንዲያከብር የሚያግድ ምንም ምክንያት የለም።

የጊዜ ጉዳይና የሚመራው አካል በሀገርቱ ሕገ መንግስት አውጆ በዓሉ ሀገራዊ ሆነው እንዲከበር ከመደረጉ ውጪ የሌሎች ባህል፣ ወግ፣ ቋንቋ፣ በየአካባቢው የሚከበረው ዘመን መለወጫ እኩል መሆኑን መረዳትና መገንዘብ የግድ ይላል።

የዎላይታ ህዝብ የጊዜና ወቅት አቆጣጠር በጨረቃና በፀሐይ (Luno-solar) የሚሰላ እንደሆነ ጥናቶች ብጠቁሙም ከጥንት ጀምሮ በጨረቃ እንደሚቆጠር ብዙ ምንጮች ይጠቁማሉ።

ጊፋታ ደግሞ የዎላይታ ብሄር ዘመን መለወጫ በዓል ነው። ጊፋታ ማለት የመጀመሪያ አዲስ ዓመት ወር ነው። ጊፋታ በዎላይታ ብሄር አቆጣጠር መሠረት የሚከበረው ከመስከረም 14-20 በሚውለው ዕሁድ ይሆናል።

በዚሁ ቀመር መሠረት የዘንድሮ የዎላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ እሁድ መስከረም 20/2016 ዓ.ም ይሆናል።

ማንነቱን ማክበርና ዕሴቶችን መንከባከብ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው❗️ራስን መሆን ሌላውን ማክበር ነውና ሁላችንም በየራሳችን እንድመቅ👐

Yoo yoo Gifaataa!!!!
እንኳን ለዎላይታ ብሄር ዘመን መለወጫ በሰላም አደረሳችሁ👐 Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *