የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከሰባ በላይ በዎላይታቶ ቋንቋ የሚያስተምሩ አገልጋዮችን አስመረቀች።

በዎላይታቶ ቋንቋ ትምህርተ ወንጌል የሚሰጡ 70 ወጣት ደቀመዛሙርት በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የዎላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በቀን 20/1/2016 ዓ/ም መመረቃቸው ተገልጿል።

በዳሞት ጋሌ ወረዳ ካሉት ገዳማትና አድባራት የተወጣጡ ለ3ወራት ቀንና ማታ ትምህርተ ወንጌል፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ነገረ ክርስቶስ፣ ነገረ ማርያም፣ ነገረ ቅዱሳን፣ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንና ቅዳሴ ሲማሩ የቆዩ 70 ወጣቶች መመረቃቸውን ከቤተክርስቲያኗ የተላከልን መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት በዎላይታቶ የተዘጋጀ የሁለት ዘማሪያን መዝሙር ምርቃት በኦቶና ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን መመረቁ ተነግሯል።

ቤተክርስቲያኗ ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ የመጣውን የምዕመናን በራስ ቋንቋ አገልግሎት የማግኘት ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም ከመረጃው የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለማውቅ ችሏል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *