ገና ሳይደራጅ የመፍረስ አደጋ የተጋረጠበት “ደቡብ ኢትዮጵያ” በተባለ ክልል ላይ በግለሰቦች መካከል ከፍተኛ የስልጣን ሽኩቻ መቀጠሉ ተገለፀ።

በአመራሮች መካከል”ክልሉ እውን እንዲሆን በታገልነው ልክ ስልጣን አልተሰጠኝም፤ የህዝብ ውክልናም በተገቢው ተግባራዊ አልሆነም” የሚሉና ስራ ሳይሰራ የመንግስት ገንዘብ ህጋዊ አሰራር ሽፋን በማድረግ እየበዘበዘ ይገኛል” ስል አንድ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ከፍተኛ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድተዋል።

እንደ መረጃ ምንጫችን ገለፃ “በነባሩ ክልልና ዞን ውስጥ በተለያዩ ስልጣን እርከን የነበሩና በተለይም ህዝቡ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገመንግስታዊ መብት ጥያቄ በህጋዊ መንገድ ቀርበው የነበረውን ከህዝብ ፍላጎት ውጪ መንግስት በሰጠን አቅጣጫ መሠረት ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈልና ጫና በማድረግ የክላስተር ክልል እውን እንዲሆን ከፍተኛ ሚና ብንወጣም የሚገባን ስልጣን አልተሰጠንም የሹመት ሂደቱም ያንን ታሳቢ ያላደረገ ነው” የሚሉ ግለሰቦች እርስበርስ መተነኳኮስ መደበኛ የመንግስት ስራ እንዳይሰራ እንቅፋት እየሆነ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

አንድ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለገና በአዲስ ክልል ሹመት የተሰጠው ከፍተኛ የዎላይታ ተወላጅ የተፈጠረውን ሁኔታ “በተደራጀው ክልል ጉዳዮች ላይ ዉሳኔ ሰጪ የሚያስብል ቦታዎች የዎላይታ ሕዝብ ዉልክና በትክክል እንዳይኖር ተደርጓል፤ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤት የሆነው የሕዝብ ዉክልና ማንጸባረቅ ህገ መንግስታዊ ግዴታ መሆኑ እየታወቀ እውነታውን በመጣስ ህዝባዊ መሠፈረትን ያልተከተለ አመራርነት እና ህገ መንግስታዊ መርህን የናደ ሹመት በመስጠት የዎላይታን ሕዝብ አፍኗል፤ የተሾሙ ግለሰቦችም በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለላቸው በተለያዩ ጥቅማጥቅም የተሳሰሩ ናቸው፤ በአስቸኳይ የእርምት እርምጃ ካልተወሰደ ክልሉ ገና ሳይመሰረት የመበታተን አደጋ ተጋርጦበታል” ስሉ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ምንጫችን እንደገለፀው “በአሁኑ ወቅት በአስተባባሪ ደረጃ የተሾሙ አመራሮች ሆነ ሌሎች መስሪያቤቶች የተመደቡ የስራ አመራሮች ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት ይቅርና እርስበርስ መስማማት አቅቷቸው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ህብረተሰቡ አገልግሎት እንዳያገኝ እንቅፋት እየፈጠረና ተጨማሪ የመልካም አስተዳደር ችግር እየፈጠረ ነው” በሚል ሁኔታውን አስረድተዋል።

በተዋቀረው አዲሱ ክልል መዋቅር አንድ በነባሩ ክልል ሰራተኛ የነበረ ግለሰብ ከእንደገና ሲዋቀር ያመጣው ጉዳት ሲያስረዳ “እስካሁን ወደተመደብነበት ቦታ አልሄድንም፣ እንድንመጣ የሚጠይቅም የለም፣ በየመስሪያ ቤት ወሳኝ የተባሉ ፋይናንስ አይነት ብቻ ሰራተኞች እንዲገቡ ተደርጎ የመንግስት ገንዘብ የተለያየ ምክንያት እየተፈጠረ እየተበዘበዘ ነው፥ የሚመለከተው አካል ካለ በአስቸኳይ ጠልቃ እንዲገባ” በሚል ጠይቀዋል።

ከመንግሥት ሰራተኞች እንግልት፣ ከህዝብ መንግታዊ አገልግሎት ለማግኘት ከቦታ ወደ ቦታ ግዜ፣ ገንዘብና ጉልበት አውጥቶ ከመንከራተት ጩሄት በተጨማሪ ሰሞኑን በተፈጠረው “ክልሉ እውን እንዲሆን በታገልነው ልክ ስልጣን አልተሰጠኝም” የሚሉ ግለሰቦች በፈጠሩት ውዝግብ ምክንያት ህብረተሰቡ መንግስታዊ አገልግሎት ለማግኘት እየተሰቃየ ስለመሆኑም አክለው ተናግረዋል።

የአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በዋልታ ቴለቪዥን መስኮት በቀረበበት ወቅት ተደረገ የተባለውን ሪፈረንደም አስመልክቶ በሰጡት ሀሳብ “ህዝቡ የፈለገውን ነው ያደረግነው” በማለት የገለጸበት መንገድ የዎላይታ ህዝብ ራስን በራስ ለማስተዳደር የከፈለውንና እየከፈለ ላለው መስዋዕትነት ክብር ያለመኖሩን የገለፀበት መሆኑና “የተደራጀው አደረጃጀት የዎላይታን ህዝብ ከወትሮ በበለጠ ለፖለቲካዊና መዋቅራዊ ምስቅልቅል የሚዳርግ ከመሆኑም ባሻገር የዎላይታን ህዝብ ክብርና ታሪኩን የማይመጥን የዜሮ ውጤት ጨዋታ መሆኑን ሁሉም ዎላይታ አውቆ የዎላይታን ህዝብ የሚመጥንና በህገመንግስቱ የተረጋገጠለትን መብት ለማስከበር ህዝባዊና ሰላማዊ ትግሉ አጠናክሮ እንድቀጥል የከበረ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ስሉ አቶ ጎበዜ ጎኣ የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር መግለፃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *