በአፍሪካ ከፍተኛ የቤት እጦት ካላቸው 10 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ 6ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አንድ ጥናት አመላከተ።

የአለም ህዝብ መረጃ እንደሚያመለክተው እየተገባደደ በሚገኘው ፈረንጆች 2023 ከፍተኛ የቤት እጦት ደረጃ ካላቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝር መካከል “ኢትዮጵያ በስድስተኛ ደረጃ ከ2.6 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በቤት ችግር እጦት ምክንያት እየተሰቃዩ ነው” የምለውን ደረጃ በማስመዝገብ እንደተቀመጠች ተገልጿል።

በአህጉሪቱ ብዙ ግለሰቦች የሚኖሩበት ቤት አጥተዋል፣ በጎዳና ላይ ይኖራሉ፣ መደበኛ ባልሆኑ ሰፈሮች ውስጥ ወይም በተጨናነቁ ሰፈሮች ውስጥ እንደሚኖሩ ጥናቱ አመላክቷል።

ይሁን እንጂ በአፍሪካ ያለው የቤት እጦት መጠን በአንዳንድ አገሮች ሰዎች በአመጽ ወይም በማህበራዊ ፖለቲካዊ ስደት ምክንያት ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ስለሚገደዱ እንዲሁም በታጠቁ ቡድኖች ግጭት በፈጠረው የውስጥ መፈናቀል ችግሩን ማባባሱንም አብራርቷል።

በአፍሪካ በተለይም “በኢትዮጵያ የቤት እጦት መንስኤ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣ ስራ አጥነት፣ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀል፣ ፖለቲካዊ እና ህጋዊ ተግዳሮቶች ነው” ስል ቢዝነስ እንሳይደር አፍሪካ በድረገጹ አስነብቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: