“ጋሞ አመራሮች ትዕዛዝ” በአርባምንጭ ደረቅ ፓሊስ ጣቢያ ከሁለት ወር በላይ ታስሮ የነበረ የደቡብ ምዕራብ ዕዝ አዛዥ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ መለቀቃቸው ተገለፀ።

ኮሎኔል ገብሬ ግንባሬ ከሁለት ወራት በላይ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በግፍ ከታሰሩበት አርባምንጭ ከተማ ሴቻ ደረቅ ፓሊስ ጣቢያ በነፃ የተለቀቁ ሲሆን ፍትህ ተዛብቶ በገዛ ወገኖቹ ክህደት ተፈፅሞባቸው ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ መታሰራቸውን ከዚህ ቀደም የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ወኪል ከቦታው መዘገቡ ይታወሳል።

ኮሌኔል ገብሬ ከአዲሱ 12ኛ ክልል መዋቅር ከመመስረቱ በፊት የጋሞ ዞን አመራሮች እና ሌሎቹ በተጠነሰሱት ህገ-ወጥ ሴራ ድንገት በአርባምንጭ ከተማ ሥራ በወጡበት “ታፊነው ከነ ሙሉ የማዕረግ ልብሳቸው ተይዘው ከታሰሩበት በትላንትናው ዕለት በመስከረም 24 /2016 ዓም በ10:00 ሰዓት ነው ከሴቻ ደረቅ ፖሊስ ጣቢያ ያለምንም ክስ በነፃ ተለዋል”

በጠቅላይ ሚኒስቴር ደ/ር ዐቢይ አህመድ ቀጥታ ትዕዛዝ የተፈቱ ሲሆን በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር የፕሮቶኮል ተሽከርካሪ በመታጀብ ነዉ ከአርባምንጭ ከተማ ሴቻ ደረቅ ፓሊስ ጣቢያ ወደ ሥራ ገበታቸዉ በክብር መሸኘታቸውን ጉዳዩን በቅርበት ስከታተል የነበረው ወኪላችን ከአርባምንጭ ዘግቧል።

ወኪላችን ከኮሌኔሉ ጋር ላፍታ ባደረገዉ ቆይታ ባደረጉት ንግግርም “የህዝብ አሌኝታ የሆነዉን ህግን በበላይነት የሚያስከብር መከላከያን የሚመራን ኮሌኔል በህገወጥ መንገድ ማሰር ህግን ከመዳፈርም አልፎ የባሰ ወንጀል እና ሽብርተኝነት ነዉ” ያሉት ኮሎኔሉ በገጠማቸዉ ያልጠበቁት ዕኩይ የወንበደዉ ስብስብ ተግባር እጅግ ማዘናቸዉንም ለወኪላችን ተናግረዋል።

አሁንም እሳቸዉ ታፍነዉ በግፍ በታሰሩበት አርባምንጭ ከተማ ሴቻ ደረቅ ፓሊስ ጣቢያ በጋሞ ዞን አርባምጭ ዙሪያ ወረዳ ከሁለት መቶ ሃምሳ በላይ ሠላማዊ የሻራ ቀበሌ ነዋሪዎች በከባድ አፈና በእስር እየተሰቃዩ መሆኑን መታዘባቸዉን ገልፀዉ በቀጣይም ለተበዳዮቹ ፈጣን መፍትሄ ከመንግስት እንዲሰጣቸዉ እንደሚታገሉላቸዉም ያረጋገጡት ኮሎኔል ገብሬ ለተሰጣቸዉ ፍትሃዊ ምላሽም ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን እና ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን አመስግነዋል።

“ኮሎኔል ገብሬ ግንባሬ ከ1985 ዓ.ም ጀምረው የኢፌድሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በሚታገሉበት በተለያዩ ግንባሮች በጀግንነት ለአገር ባበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋፆ በሠራዊቱ በተለያዩ መዋቅሮች የማዕረግ ደረጃቸውን በማሳደግ የኮሎኔልነት ማዕረግ ከመንግስት እዉቅና በክብር የተጎናፀፋ ታማኝ ለሀገር ዋጋ የከፈለ መሆኑ እየታወቀ ህግን ባልተከተለ ቦታ መታሰሩ በዕዙ የሚገኙ ሁሉንም አባላት ያስቆጣ አስነዋሪ ተግባር ነው” ስሉ ቤተሰቦቹና የሙያ አጋሮቹ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የጋሞ አከባቢ ወኪላችን በመግለፅ ጥሪ አቅርቧል ብለን መዘገባችን ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: