የሀገር መከላከያ አባል የሞት ዜና ለቤተሰቦቹ እንዳይደርስ ባደረጉ አካላት ላይ እርምጃ ተወሰደው በተሰጠው አስቸኳይ ምላሽ መደሰታቸውን የሟች ቤተሰብ አባላት ገለፁ።

በሌላ በኩል በዎላይታ ዞን በርካቶች ልጆቻቸው በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት በሀገር መካላከያ ጎን የተሰለፉ ቢሆንም “እስካሁን ይሙቱ ይኑሩ ስለማይታወቅ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ” ሲሉ ጠይቋል።

በዎላይታ ዞን ገሱባ ከተማ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባል የሆነው ሟች መ/አለቃ ያዕቆብ ዮሐንስ በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት መስከረም 13/2015 ዓ.ም ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ ከመከላከያ ሚኒስትር በአድራሻው ቤተሰብ የለቅሶ ስነስርዓት እንዲያከናውን በሚደርገው አሰራር ወደ ሟች መ/አለቃ ያዕቆብ ዮሐንስ ቤተሰብ መርዶ እንዲነገራቸው ወደ ዎላይታ ዞን ገሱባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ለሟች ቤተሰብ እንዲያደርሱ የመርዶ ደብዳቤ ቢላክም ግለሰቦቹ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ደብደቤውን በመደበቅ የውሸት ሰነድና ሰው አዘጋጅቶ በሌላ በሌላ ወረዳ እንዳለ በማስመሰል ያደረጉት ሙከራ መጋለጡን ተከትሎ በርካታ ተመሳሳይ ማጭበርበር መፈፀሙን የሚገልጽ መረጃ መውጣቱንም መዘገባችን ይታወሳል።

ለሟች ቤተሰብ ከመከላከያ ሚኒስትር የሚሰጠውን ካሳ በማጭበርበር ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል በማሰብ ወደ ገሱባ ከተማ በአድራሻው የመጣውን ደብዳቤ “በስህተት ነው የመጣው አድራሻው ካዎ ኮይሻ ወረዳ ላሾ ቀበሌ ነው” በሚል የውሸት ሰነድና ቤተሰብ አዘጋጅቶ ከመከላከያ ሚኒስትር የሚሰጠውን ካሳ ለመውሰድ ሁሉንም ነገር ከጨረሱ በኃላ መደረሱን ከመከላከያ ሚኒስትር የደረሰው መረጃ ጠቅሰን መዘገባችን ተከትሎ በሁለት ወረዳ ብቻ ከ28 በላይ ተመሳሳይ ማጭበርበር መፈፀሙንም የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በድጋሚ ማጋለጡ ይታወሳል።

የሟች ቤተሰብ አባላት የተፈጠረው ነገር እጂግ አሳዛኝና የሰው ልጅ እንዲህ ያደርጋል ተብሎ የማይታሰብ ነውር ተግባር መሆኑን በመግለፅ አሁን ላይ የለቅሶ ስነስርዓት በባህሉ መሠረት የተፈፀመ ሲሆን በተለይም የገሰባ ከተማ ከንቲባ አቶ ደጉ ደሳለኝ በቁርጠኝነት እውነት እንዲወጣ ለሟች ቤተሰብ ተገቢው ካሳ እንዲከፈል በቅርበት ተከታትለው ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል።

የገሱባ ከተማ ከንቲባ ለሟች ቤተሰብ አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት ባለፈ የሀገር መከላከያ አባል የሞት ዜና ለቤተሰቦቹ እንዳይደርስ ያደረገ የፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊን ከአመራርነት በማገድ እንዲሁም ሌሎች በሂደቱ የተሳተፉት በህግ እንዲጠየቅ እየተደረገ እንደሆነ የሟች ቤተሰቦቹ ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት ከገሱባ ከተማ እና ካዎ ኮይሻ ወረዳ ብቻ ከ28 በላይ የሀገር መከላከያ አባል የሞት ዜና ለቤተሰቦቹ እንዳይደርስ በማድረግ “ያልተገባ ጥቅም አግኝቷል” የሚሉ ቤተሰቦች ክስ መስርቶ እየተከታተሉ እንደሆነና ከሌሎች አከባቢም በርካቶች ልጆቻቸው በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ይሙቱ ይኑሩ ስለማይታወቅ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ በሚል ክስ ይዘው ወደ ፍርድቤት መምጣታቸውን ከፍርድቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: