


እስኪ በየመድረኩ የማይጠፉ “የዎላይታ ሽማግሌዎችንና የሀይማኖት አባቶችን” አንዴ እንጠይቃቸው👇
በየመድረኩ ከመንግሥት ባለስልጣናት ስብሰባዎችና ዝግጅቶች የማይጠፉ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ለምን በአከባቢው በሙስናና ብልሹ አሰራር የተዘፈቁት አያወግዙም❓
በአከባቢው ላለፉት አራት አመት ለህዝብ መብት ወግነው ሲታገሉ የነበሩ ከስራ ተፈናቅለው ከእነ ቤተሰቦቻቸው ለችግር ተጋልጠው ኑሮ ሲገፉ እነኚህ ዝምታን ለምን መረጡ❓ ለምንድነው ለህዝብ ስለወገኑ ብቻ ከሚወዱት አከባቢ የተለያዩ ጫናዎች በመድረሱ ከእነ ቤተሰቦቻቸው ሀገር ውስጥና ውጭ ድረስ የስደት ኑሮ እየገፉ ስለሚገኙት እውነት ለማውራት ዝምታን የመረጡት ❓

ለምንድነው በህብረተሰቡ መሃል እየኖሩ ህዝቡ ለተለያዩ መልካም አስተዳደር ችግሮች ተጋልጠው እየተንከራተተ በሚገኝበት ድምፅ ማሰማት ያልቻሉት ❓ ለምንድነው በዞኑ በተለያዩ መዋቅር ደረጃዎች የመንግስት ስልጣንን በመጠቀም የየራሳቸው የጥቅምና የጎሳና አደረጃጀት ዘርግተው ሰፊውን ህዝብ ፍላጎትና መብት በመጫን ሲያሰቃዩ መናገር ያልፈለጉት❓
በአከባቢው ሁለንተናዊ የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥና የህዝብ መብት እንዲከበር ከፊት ሆነው ራሳቸውን ሰጥተው እየተሟገቱ እስር፣ ከስራ መፈናቀልና ስደት እያስተናገዱ የሚገኙ አብዛኞቹ ገና የኑሯቸውን መሠረት ያላስተካከሉ ወጣቶች ሲሆኑ በተቃራኒው ሁሉም ነገር የተመቻቸላቸው በየመድረኩ ከባለስጣናት ስብሰባና ዝግጅት መድረክ ፊትለፊት የማይጠፉ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ለምን እምብዛም የሰፊው ህዝብ ጥቅም፣ ክብርና መብት ግድ አይላቸውም ❓
በዞኑ በፓለቲካ አካሄድ ልዩነት ምክንያት ብቻ ዳርና ዳር ሆነው የሚገኙ ወገኖች ወደ አንድነት፣ መደማመጥ፣ መተባበር እንዲሁም በጋራ ጉዳይ በሆኑ የህዝብ የልማት ፍላጎቶች ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡና በአንድነት በመሰለፍ በጎ ሚና ሊወጡ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ ሰብሳቢ ከየት ይምጣ❓

እንደሚታወቀው የዎላይታ ዞን ሁለት መቶ ሺህ የሚጠጋ ከታወቁ ከፍተኛ ዩንቨርስቲዎችና ኮሌጆች የተመረቁ የስራ አጥ ወጣቶች የሚገኙበት፣ ህፃናት በለጋ ዕድሜያቸው ከእናታቸው ተለይተው በሀገሪቱ ጎዳናዎች ሁሉ የስቃይ ህይወት እየገፉ የሚገኙት፤ ስልጣን በትውውቅ፣ በዝምድና እንዲሁም በጥቅማጥቅም ትስስር የተመሠረተ በመሆኑ በከፍተኛ ውጤት የተመረቀ እያለ የአመራር ዘመድ ያለው ያለውድድር በግዢ ወሰቀት ያመጣ የሚቀጠርበት፣ ጉቦና ብልሹ አሰራር የተለመደ አሰራር እየሆነ የመጣበት ሁኔታ ውስጥ መኖሩን እያወቁ ለምን ለምን ብለው አይናገሩም❓
በየመድረኩ ከፊት የማይጠፉ እነኚያ “የዎላይታ ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች” ተወካዮች ተብለው በየመድረኩ ከመንግሥት ባለስልጣናት ዝግጅቶችና ስብሰባዎች ሁልጊዜ የማይጠፉት “በተጨባጭ የህዝብ በደል እየሰሙ ለምን እንዳልሰሙ ዝምታን በመምረጥ እስከመቼ ይቆያሉ” በሚል የ Wolaita Times ሚዲያ እንድ የአንድ ህዝብ ጉዳይ በቅርበት የሚከታተል ሚዲያ ለምን ብሎ ይጠይቃል❗️ ግን ለምን ❓