የአዲሱ ክልል ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ ዝግጅት የተለያዩ ከፍተኛ አመራሮችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በዎላይታ ሶዶ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

“ደቡብ ኢትዮጵያ” በሚል በቅርቡ የተመሰረተው ክልል በመጪው ህዳር 8/2016 ዓ.ም ከፌደራል፣ ከክልሎች፣ ከከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከሀገሪቱ ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ አመራሮችና ታዋቂ ግለሰቦች በሚገኙበት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ላይ በይፋ እንደሚካሄድ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ከልዩ ወረዳነት ወደ ዞንነት የተዋቀሩ አምስት የዞን መዋቅሮችን ጨምሮ አስር ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በአንድነት የመሰረቱት “ደቡብ ኢትዮጵያ” የተሰኘ ክልል መንግስታዊ አገልግሎቶችን በተለያዩ ቦታዎች ጀምሯል ቢባልም ከተወሰኑት ውጪ አብዛኞቹ በሙሉ አቅማቸው አለመጀመራቸው በህብረተሰቡ ከፍተኛ ቅሬታ እያስተናገደ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።

ህዳር 8/2016 ዓ.ም የአስተዳደርና የፓለቲካ ማዕከል በሆነችሁ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ክልሉ በይፋ ስራውን ለመጀመር በሚያበስረው ዝግጅት ላይ “ለተለያዩ ልማት ስራዎች የሚውል ገቢ ከፌደራል፣ ከክልሎች፣ ከከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከተለያዩ ቦታዎች ከሚመጡ አመራሮችና ታዋቂ ግለሰቦች ለማግኘትና ክልሉ በሙሉ አቅም ስራውን ለመጀመር የሚያስችል ይፋዊ ዝግጅት ነው” በሚል የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ታማኝ ምንጭ አስረድተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *