

የዚህች እናት ምስል ከማታ ጀምሮ በሚዲያ ስዘዋወር አይቼ እንቅልፍ ነስቶኛል። ፊቷ ላይ የሚታየው የምጥ ስቃይ እና ለመጓዝ የተጠቀመችው ከመንገዱ ጋር ተዳምሮ ሌላ ስቃይ ሆኖባት ሴት ሆና የተፈጠረችበትን ቀን የረገመች ይመስላል።
ይህች እናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ ከላይማ ፃላ ጤና ጣቢያ ወደ ሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ሪፈር ተደርጋ፣ አምቡላንስ ስለሌለ የሁለት እግር ሞተርሳይክል ለመጠቀም ተገዳለች፤ መንገዱም እንኳን በምጥ የተያዘች እናት፣ ጠናማው አንዴ ከሄደ ሳምንት ይታመማል ብል ማጋነን አይሆንብኝም።
ይህች እናት ያ የላይማ ፃላ ፃይና፣ ያላነሰ ወደ 45 Km መንገድ፣ ህይወቷን ለማትረፍ በዚህ መልክ (ከታች እንደሚታየው) ተጉዛለች።


ለመሆኑ በዚህ ሁነታ የተጓዘችው እናት ህይወቷ ተርፎ ይሁን? ህፃኑስ? በንደዚህ አይነት መንገድ በምጥ የተያዘች or any pregnant mother በሞተር ሳይክል ከተጓዘች ያለው መዘዝ (consequences) ብዙ ነውና ትቸዋለሁ።
በዞናችን አብዛኛው አከባቢ የጤና ጣቢያ መስጠት የነበረበትን አገልግሎት የማይሰጥ እና ለስሙ ያለ ስለሆነ ህዝቡ በተለያየ ሁነታ ለሞት እየተዳረገ ነው። የጤና ባለሞያ የ14 ወር የትርፍ ሰዓት ክፊያ ባለመከፈሉ ከሥራ ሰዓት ውጭ ያለው አገልግሎት ተቋርጧል። ለ Wolaita Times በውስጥ የተላከ መልዕክት
በሌላ ዜና በትናንትናው ዕለት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ከጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ወደ ዎላይታ ሶዶ 40 ኪ.ሜ ገደማ ያለ አዲሱ አስፓልት ላይ የዋጌሾ ማዞሪያ ድልድይ ተብሎ የሚጠራው ትናንት ማታ ምክንያቱ ለጊዜው ባልታወቀ ሁኔታ ተሰብሮ እስካሁን ምንም አይነት ጥገና ሆነ ተለዋጭ መንገድ ባለመከፈቱ መንገደኞችና አሽከርካሪዎች ለእንግልት መደረጋቸውንና ከአከባቢዎች ወደ ክልሉ ዋና ከተማ ዎላይታ ሶዶ ከተማ የሚደረግ ጉዞ ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱ በርካታ ማህበራዊ ቀውስ የሚያስከትል በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ መጠየቃቸውን ከቦታው ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰውን መረጃ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።