ኃይለማርያም የጥሩ ስብዕና ክህሎት ያለዉ፣ ትሁትና ከሰዎች ጋር ወዳጅነት መፍጠር የሚችል፣ ከየትኛውም ሰዉ፣ ምናልባትም ከሱ በታች ካለ ሰዉም ቢሆን ትምህርት ከመቅሰም የማይቦዝን ልዩ መሪ ነው” – አቶ ጌታቸው ረዳ ስለ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከተናገሩት

አቶ ጌታቸው ረዳ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር ከነበሩበት ከ 97 ምርጫ በሁዋላ ወደ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ተመድበዉ፣ አዲስ አበባ ከመጡ በሁዋላ በወቅቱ ተነባቢ በነበረዉ በአዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ የኢህአዴግን ፖሊሲዎች እየተከላከሉ ይጽፉ ነበረ። በተለይ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩባቸው ዓመታት ከኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በቅርበት ሰርተዋል። የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር እና የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ልዩ አማካሪ እንደነበሩም ይታወሳል። እሳቸዉም ከኃይለማሪያም ጋር ተቀቀራራቢ academic back ground ያላቸዉ ሲሆን ወደፖለቲካ የገቡትም ከዩኒቨርስቲ ነው።

VOA ኃይለማርያም ደሳለኝ ከ2010 ጀምሮ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር እንደነበሩ ጠቅሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ በወቅቱ ለተወሰኑ ዓመታት አብሯቸዉ የሰራዉን የአቶ ጌታቸው ረዳን ምስክርነት አቅርቦ ነበር። አቶ ጌታቸዉም “ኃይለማርያም የጥሩ ስብዕና ክህሎት ያለዉ መሪ ነው። በጣም ትሁትና፣ ከሰዎች ጋር ወዳጅነት መፍጠር የሚችል ሰዉ ነው። ከየትኛውም ሰዉ፣ ምናልባትም ከሱ በታች ካለ ሰዉም ቢሆን ትምህርት ከመቅሰም የማይቦዝን ሰዉ ነው።

ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር የጋራ መግባባት ለመፍጠር የሚጥር ሰዉ ነው። ቆፍጠን ማለት ሲኖርበት ያንንም መሆን የሚችል ሰዉ ነው። ኢትዮጵያዉያን መቼ ቆፍጣና መሆን እንዳለባቸዉ ያዉቃሉ። እንደዉም እዚህ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር የመንግሥት መዋቅር ዉስጥ የምንገረምባቸዉ አጋጣሚዎች አሉ። እርግጠኛ ሆኜ የምነግርህ፣ አስፈላጊ ሲሆን፣ ኃይለማርያም እንደማንኛቸዉም፣ እሱም ቆፍጣና ሊሆን ይችላል።” በወቅቱ BBC ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ደግሞ ኃይለማርያም በሚመሩት መሥሪያ ቤት ወደ አምልኮት የተጠጋ አሸርጋጅ አንጃ የመፍጠር ባህሪ እንደሌላቸዉ ጠቅሰዋል።

ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን ሲወርዱ የኢህአዴግ እና የህውሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ የነበሩት ጌታቸው ረዳ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት “ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በነበረው የስልጣን ሽግግር ወቅት የወንበሩ ፈላጊ እና እኔ ነኝ አዋቂው የሚለው ሰው ቁጥር በመብዛቱ ይህ ችግር ተፈጥሯል፡፡

የአስተሳሰቡ ተረካቢ እኔ ነኝ ዋነኛ ባለቤት ከእገሌ በበለጠ የማውቀውና የምረዳው እኔ ነኝ ባዩ በመብዛቱ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስራቸውን በሚገባ እንዲሰሩ ከመርዳት ይልቅ ሙከራዎቻቸውንና እንቅስቃሴዎቻቸውን የመንቀፍ ነገር በዝቶ ነበር።

ኢህአዴግ ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በአንድነትና በተደራጀ መንገድ ለስኬታቸው ከመንቀሳቀስ ይልቅ ነጥብ በማስቆጠር ላይ ያተኮረ ነበር። የኢህአዴግን አላማዎች ተግባራዊ ለማድረግና አንድ ወገን ለመስራት ይጠበቅብናል የሚለውን መርህ የሳተና የጎዳ ነበር ፡፡” ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: