በብልሹ አሰራር የቆሸሽዉን የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ገጽታ የማደስና የመገንባት ኃላፊነት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ አሳሰቡ።

የፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ፣ የመብት ተሟጋችና የቀድሞ የድላ ዩንቨርስቲ መምህር ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች በብልሹ አሰራር ምክንያት ከስልጣናቸው መባረራቸውን ተከትሎ ከዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ ምክር አዘል ማስጠንቀቂያ ለሚመለከታችው ሁሉ አስተላልፈዋል።

ረዳት ፕሮፈሰር አሰፋ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ሲሰጡ “ታከለ ታደሰና ግብረአበሮቹ በስልጣን ዘመናቸዉ የፈለጉትንና የወደዱትን ለማድረግ አገራዊ፣ ክልላዊና ዞናዊ የፖለቲካ ዉጥንቅጥ፣ ደካማ፣ አድርባይ፣ ጥገኛ ቦርድ፣ አካዳሚክ ካዉንስልና ሴኔት እንደዚሁም አብላጫዉ የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ (በተለይም የአካዳሚክ ስታፍ) የማምለጥ ባህሪ እንደ ምቹ አጋጣሚ ተጠቅመዋል” በሚል አብራርተዋል።

“ሙስናና ብልሹ አሰራር በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች አልነበረም ማለት አይደለም። ነገር ግን በሌሎች የኢትዮ-ዩኒቨርሲቲዎች ባልተለመደ መልኩ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ አሉታዊ ገበናዎች ብቻ በየዕለቱ በማህበራዊ ሚዲያዎች ይሰጣ ነበር” ስሉ የመብት ተሟጋቹ ሁኔታውን ገልጸዋል።

እንደ ረ/ፕሮፈሰሩ ገለፃ “በማህበራዊ ሚዲያዎች ስለ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሙስና ቅሌትና ብልሹ አሰራር የማይራገበዉ ችግሮችን በየዩኒቨርሲቲዉ መደበኛ ቻናል በዉይይት፣ በክርክር ብሎም በግምገማ የሚፈታበት አሰራርና ልምድ ስላለ ነዉ” በሚል አብራርተዋል።

ሁለተኛዉና ዋነኛዉ ምክንያት የየዩኒቨርስቲዉ ማህበረሰብ ተቋማዊ ችግሮችን በፌስቡክ መንደር በመዘርገፍ መፍትሔ ማግኘት የማይቻል ከመሆኑም በላይ ተቋማዊ ጉዳት የሚያስከትልና የዩኒቨርሲቲውን ገጽታ የሚያበላሽ መሆኑን በመገንዘብ የተቋማዊ ባለቤትነት የሚሰማቸዉ በመሆኑ እንደሆነ የፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ፣ የመብት ተሟጋችና የቀድሞ የድላ ዩንቨርስቲ መምህር ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ ያብራሩት።

“የተቋማዊ ገጽታ ተበላሸ ማለት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ገጽታ ይበላሻል። በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለጠፉ፣ ብሮድካስት የሚደረጉ መረጃዎች፣ ዘገባዎች ዓለማቀፍ፣ አገርአቀፍ፣ ሎካል ማህበረሰብ አቀፍ ተደራሽነት ያላቸዉ መሆኑ አይካድም። መጥፎ ገጽታዎቹ ብቻ በብዙ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በተከታታይ ብሮድካስት የሚደረግበት ዩኒቨርስቲ ተቋማዊ ሕልዉናዉ አደጋ ዉስጥ ይገባል” ስሉም ረ/ፕሮፌሰሩ ስለሁኔታው አሳሳቢነት ተናግረዋል።

“እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ የተመሠረቱበትን ሶስቱን ዋና ዋና ተልዕኮዎችን በአግባቡ በመወጣት ለብሔራዊ፣ ክልላዊና አከባቢያዊ ሁለንተናዊ የልማት ሂደት ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ በሚል በየዓመቱ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ኢንቬስት የሚያደርገዉ መንግስታዊ አካል አሉታዊ እርምጃ ሊወስድ ይችላል” ብለዋል።

“በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲዎችን የሳይንሳዊ ምርምር፣ ዘመናዊና ችግር ግኝቶች፣ የእውቀት ማዕከላት ናቸዉ ብሎ የሚያምነዉ ተራዉ ማህበረሰብ አደገኛ የጋርዮሽ አመለካከት ሊያዳብር እንደሚችል መገመት እንደሚቻል በመግለፅ በተጠቃሽ ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ ባሉ አከባቢዎች የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ስለ ዩኒቨርስቲ ትምህርት የተዛባ ወይንም አሉታዊ እይታ ያዳብራሉ” በሚል አብራርተዋል።

ረ/ፕሮፌሰሩ ከዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ያደረጉትን ቆይታ ሲያጠቃልሉ “አዳዲስ መምህራን፣ ተመራማሪዎችና ተማሪዎች ወደ ተጠቃሹን ዩኒቨርሲቲ ለመቀላቀል ደስተኛ- ፈቃደኛ አይሆኑም። ከተጠቃሽ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዉ የሚወጡ ተማሪዎች ሀፍረት ይሰማቸዋል። እነኚህን ምሩቃን የመቀጠር ዕድላቸዉ ዉስን ይሆናል። በጣም ብዙ ሕዝብ በሚጠቀማቸዉ ማህበራዊ ሚዲያዎች በማወቅ ባለማወቅ የቆሸሽዉን የዩኒቨርስቲ ገጽታ ማደስ-መገንባት በጣም ከባድ ይሆናል። በመሆኑም ትኩረታችን የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ገጽታ ማደስ–መገንባት ላይ ያገባኛል የሚል ሁሉም ትኩረት እንዲያደርጉ” በሚል ጥሪ አቅርበዋል።

የፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ፣ የመብት ተሟጋችና የቀድሞ የድላ ዩንቨርስቲ መምህር ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ ላለፉት አራት አመታት በዎላይታ ህዝብ የሚደርሰውን ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ መብት እንዲከበር በተለያዩ መንገዶች በመታገሉ ከስራ ተፈናቅለውና በተደጋጋሚ ለእስር ከተዳረገ በኃላ ከእነ ሙሉ ቤተሰብ ለችግር ተጋልጠው የመከራ ህይወት እየገፉ እንደሆነ ይታወቃል።

1 thought on “በሙስና የቆሸሽዉን ዩኒቨርስቲ ገጽታ የማደስ ተግባር ቅድሚያ ይሰጥ” ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ

  1. ቅድሚያ የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ! ለወላታ ሶዶ ዩንቨርስቲ በ2014 ዓ.ም በRemedal ተማሪዎች በኩል አስተያየት ለመስጠት ነው።በዚህ ዘመን የተማሪዎች ህይወት እንዳይበላሽ መጠንቀቅ የሁላችን ግዴታ ነው።እንደዚህ ስባል ደግሞ ያልሰሩትን አሳልፏቸው እያልኩ አይደለሁም። አምና በወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ በ Regular ሆነ በ Weekend Remedial ተማሪዎች እንዳሉት ይታመናል ቢሆንም ተማሪዎች በ70%ቱ ላይ የእርማት ችግር ይሁን በሌላ ጉዳይ ይሁን(ለበጀት) ውጤታቸው ላይ ትልቅ ችግር እንዳለበት ተማሪዎች በአካልም ሆነ በSocial media ተማሪዎች ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል ግን የግቢው ምላሽ ተማሪዎችን የማያረካ ሆኖ መታየት አሳሳቢ ሆኖልናል ።ምላሾቻቸው 70%ቱ እንደገና አይታይም ነው እንዴት ልሆን ይችላል?
    ስለዚህ ውድ እህት ወንድሞቼ ስለነገ ሁላችንም አናውቅም ለተበደሉት ተማሪዎች ሚዛናዊ ስራ እንድሰራ ሁላችንም እንድንነሳ አሳስባችኋለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *