የታላቁ ኦሮሞ ህዝብ የጀግንነት ተምሳሌት የነበሩ የጅማው ንጉሥ አባጅፋርና የዎላይታው ንጉሥ/ካዎ ጦና እጅግ የጠነከረ መልካም ግንኙነት በመኖራቸው ከጓደኝነትም አልፎ አማቾች ነበሩ። አንዳቸው አንዳቸውን ለማስገበር ብሎ አንድንም ጦርነት አላካሄዱም። ዛሬ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር የዎላይታ ህዝብ በኦሮሚያ ክልል እንደ ቤታቸው አድርገው የሚኖሩበት ምስጥርም ከዚሁ የመሪዎቻቸው ከገነቡት ታሪካዊና ከማይበጠስ ወዳጅነት የመነጨ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክራሉ።

በተጨማሪም ያኔ የተገነባው የዎላይታዎች የአንድነት እና ከየትኛውም ህዝብ ጋር ተስማምተውና አብሮ ሰርተው ጠንክረው የመኖር ስነልቦና የተገነባው በንጉሥ ጦና ጊዜ መሆንንም የታሪክ አዋቂዎች ያስረዳሉ።

ይሄ ስነልቦና ዎላይታዎች ከኢትዮጵያዊያን🇪🇹ወንድሞች ጋር ስቀላቀሉም ሳይቸገሩ እንዲያውም ለሌሎች በአንድነት እና አብረው በመኖር ረገድ ተምሳሌት በመሆን የዘለቁበት ምስጥርም ያኔ በተገነባው ከሌሎች ህዝቦች ጋር አብረው ተስማምተው ለመኖር ያደረጉበት ጠንካራ የካበተ ልምድ መሆኑም ይነገራል።

በነገራችን ላይ ንጉሥ ጦና ጋጋ ዎላይታ ሀገር በነበረበት ወቅት ከጅማው ንጉሥ አባ ጅፋር ጋር የነበረው ጠንካራ ዲፕሎማሲ ብቻ ሳይሆን ከአጎራባች ህዝቦች ጋር፣ አልፎም በሀገር እና ሀገርአቀፍ ደረጃ የነበረው አንድነት፣ አብረው መኖር፣ የህዝቦች ወዳጅነትን ለማጠንከር የተወሰዱ ስታራቴጂክ መንገዶች ዛሬ ዘመናዊ አሰራር በሰፈነበት ወቅትም ጠቃሚ መሆናቸው ይነገራል።

ካዎ (ንጉሥ) ጦና ጋጋ እና ንጉስ አባ ጅፋር አማቾች ከመሆናቸው በላይ የልብ ወዳጆችና ጓደኛሞች ነበሩ። ከዚህ በተጨማሪ #ዎላይታና #ኦሮሞ የምያመሳስለው ተፈጥሯዊ ጉዳይ፦ ደግነት፣ የዋህነት፣ በጎነት፣ ሰው ወዳድነት እንዲሁም የሰው አክባሪነት በፉጹም ያመሳስላቸዋል ስል የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።

በሚሊዮን የሚቆጠር የዎላይታ ህዝብ በኦሮሚያ ክልል እንደ ቤታቸው አድርገው የሚኖሩበት እየመራ የሚገኘው ፕረዚዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ በሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ ለመንግስታዊ ስራ ወደ ዎላይታ በዛሬው ዕለት ሲገቡ የተለየ ደማቅ አቀባበል በአከባቢው አመራሮችና ነዋሪዎች የተደረገበት ምስጥርም ከዚሁ የመሪዎቻቸው ከገነቡት ታሪካዊና ከማይበጠስ ወዳጅነት የመነጨ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *