07/13 ዓ ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

የቀድሞ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ፣ አቶ ጎበዜ ጎዳና ም/አስተዳዳሪ እና አቶ ተከተል ጎኣ (የቀድሞ የዞኑ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ) ላይ በቀረበው አንድ ክስ ማለትም “የመንግስትን ስልጣን አለአግባብ በመገልገል ለዎላይታ ልማት ማህበር፣ ለዎላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ እና ለንግድ ምክር ቤት ከዞኑ አስተዳደር የተሰጠው ድጎማ ገንዘብ አግባብነት የለውም” በማለት ተጨማሪ ክስ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተመሰረተው ላይ ብይን ለመስጠት ለቀን 17/06/2013 ዓ.ም ተቀጥሮ የነበረው “በድምጸ መቅረጫ የተቀዳው የምስክሮች ቃል ተገልብጦ አላለቀም” በማለት ለቀን 01/07/2013 ዓ.ም መቀጠሩን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።