ከዎላይታ አራዳ ደብረገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤትክርስቲያን አንድ ቄስ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ይዘው መጥፋቱ ተገልጿል።

በላፈው ሳምንት በዎላይታ ሶዶ ከተማ አራዳ ደብረገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ቤትክርስቲያን የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ የነበሩት ካህን/ቄሰ አወቀ ምህረት ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የቤተክርስቲያኗ ተቀማጭ የሆነውን ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ይዘው መጥፋታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ገንዘብ ይዘው ከጠፉ ቄስ ጋር ለረጅም ጊዜ ሲያገልግል የነበረው አንድ ቄስ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ እንደገለፁት “ካህኑ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የቤተክርስቲያን ተቀማጭ ገንዘብ የነበረውን በማጭበርበር ከተሰወረ ሳምንት ሆኗል” ብለዋል።

አሁን ላይ ቤተክርስቲያኗ ገንዘብ አጭበርብረው የተሰወረውን ቄስ/ካህን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ መሆኗን በመግለፅ ለጊዜው በግለሰቡ ባንክ ታግዶ ቀጣይ ስራዎች እየተከናወነ ስለመሆኑም አስረድተዋል።

ቄሱ ከጥሬ ገንዘብ በተጨማሪ ሌሎች ውድ የሆኑ የቤተክርስቲያኗ እቃዎችን ይዘው እንደተሰወሩ፣ ከየትኛው አካል ጋር ለምን አላማ ተባብረው ያንን አሳፋሪ ተግባር እንደፈፀመ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የማጣራት ተግባርም እየተሰራ ስለመሆኑም የመረጃ ምንጫችን አክለው ገልጸዋል። ዘገባው በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ ተጠናቅሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *