ለህዝብ የመጣውን ወደ መቶ ኩንታል የሚጠጋ ስኳር የሰረቁ ሌቦች በዎላይታ ተጠያቂ አልሆኑም ❗️

ለዎላይታ ህዝብ ከመንግስት በድጎማ ሲቀርብ የነበረዉን የስኳር ስርጭት በህገ ወጥ መንገድ በግለሰቦች እጅ መግባቱን በዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ እርምጃ እንዲወስድ ለዞኑ ኅብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት በጻፈዉ ደብዳቤ መነሻ ጦና ሸማቾች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኦዲት ተደርጎ ወደ መቶ ኩ/ል የሚጠጋ ስኳር በዩኒየኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታረቀኝ ጃርሳ እና በንብረት ክፍል ሠራተኞች በህገወጥ መንገድ በዘረጉት መስመር መበላቱ ተረጋግጦ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠቅላላ ጉባኤው ዉሳኔ የተሰጠ ብሆንም እስካሁን የዞኑ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ሆነ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ዝምታ መምረጣቸውን ተገቢ እንዳልሆነ ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርቧል፡፡

ከዎላይታ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዬን ለዎላይታ ዞን መሠረታዊ ፍጆታ ስኳር እያቀረበ የነበረውን በወቅቱ በተፈጠረዉ ችግር መነሻ ተብሎ ግልጽና አሳማኝ ሁኔታ ሳይፈጠር በደብዳቤ ብቻ ዉል በማቋረጥ 4ኛ ዙር ጦና ሸማቾች ህብረት ስራ ዩኒዬን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በኩል እንዲስራጭ መደረጉን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከዚህ በፊት መዘገቡ ይታወሳል።

በወቅቱ ግለሰቦች በተደራጀ ሁኔታ የውሸት ችግር እንደተፈጠረ አድርጎ በዎላይታ ገበሬዎች ዩኒዮን በኩል ለዞኑ የሚቀርበውን መሰረታዊ ስኳር ፍጆታ እንዲቆምና የዩኒየኑ ስራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ዳሳና ዋና በውሸት ክስ ከኃላፊነታቸው እንዲነሳ ከተደረገ በኃላ ዉል በማቋረጥ ጦና ሸማቾች ህብረት ስራ ዩኒዬን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በኩል እንዲቀርብ የተደረገ ቢሆንም አዲስ ወደ ኃላፊነት የመጣው የዎላይታ ገበሬዎች ዩኒዮን ስራ አስኪያጅ ከሌሎች ግብረአበሮቻቸው ጋር በመናበብ ለህብረተሰቡ የመጣውን ለግል ጥቅም ማዋላቸው በመረጃ መጋለጡን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በአከባቢው ለአብነት ይሄንን ለህብረተሰቡ የመጣውን ፍጆታ እቃ አመራሮች ሰራተኞቻቸው እና ነጋዴዎች በተደራጀ ሰንሰለት የሰረቁት በጥቂቱ ይፋ ሆኗል እንጂ በየወሩ መንግስት የህብረተሰቡን ኑሮ ሁኔታ ለማቃለል ተብሎ የሚቀርበው ዘይትና ስኳር እንዲሁም ሌሎች የፍጆታ እቃዎች የሚመለከታቸው አካላት ተገቢ የሆነ ክትትል፣ ቁጥጥርና ህጋዊ ተጠያቂነት ባለመኖሩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ከየአቅጣጫው የደረሰን ተጨባጭ መረጃ ያሳያል። በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *