አሰልጣኝና የቡድኑ አንበሎች የክለቡ አባላት የተጠቀመበትን የምግብና የአልጋ ባለመክፈላቸው በዎላይታ ሶዶ ከተማ መታሰራቸው ተገለፀ።

በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ለ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ውድድራቸውን በማከናወን ላይ የሚገኙት ካማሺ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በአክሱም ሆቴል የተጠቀሙት የምግብ ክፍያ ሁለት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ እንዲሁም የአልጋ ሁለት መቶ ሀያ ሁለት ሺህ አራት መቶ መክፈል ባለመቻላቸው በዛሬው ዕለት በፓሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ጠቅላላ ድምር አምስት መቶ አስር ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ብር በላይ ባለመከፈሉ ምክንያት የክለቡ ዋና አሰልጣኝ፥ ቡድን መሪ እና አምበሎች በወላይታ ሶዶ ከተማ ኦሞ ሼለቆ ሆቴል አከባቢ በሚገኘው መሃል (ጊዶ) ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

ባለፈው ሳምንት በዚሁ በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ለ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ውድድራቸውን በማከናወን ላይ የሚገኙት ቡሌ ሆራ እግር ኳስ ክለብ በትንሳኤ ካፌና ሬስቶራንት የተጠቀሙት የምግብ ክፍያ ከመቶ ሺ ብር በላይ ባለመከፈሉ ምክንያት የክለቡ ዋና አሰልጣኝ የሆነው ግዛው ልኬና የቡድኑ ካፒቴኖች በዋስ እንዲወጡ እና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ተደርጎ ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *