የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ አካዳሚክ ነጻነት በአድሶቹ አመራርች እየተጣሰ መሆኑ እንዳሳሰባቸው መምህራን ገልጿል።

የዩኒቨርስቲው መተዳደሪያ ደንብ እና መካከለኛና ዝቅተኛ አመራር አስያየም “በመመሪያ መሠረት በውድድር መሆን ስገባ ያለወድድር በማንአለባኝነት የቀድሞ ትውውቅ መነሻ ተደርጎ የሚሰጠው በአስቸኳይ እንዲስተካከል እንጠይቃለን” ስሉ መምህራኖቹ ቅሬታ አቅርቧል።

መምህራኖቹ በተወካዮች በኩል ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በሰጡት መረጃና ማስረጃ በቅርቡ በዩንቨርሲቲው አዲስ የተሾሙ አመራሮች እንቅስቃሴ በተመለከተ በተለይም ሰሞኑን በዩንቨርሲቲ አካዳሚክ ነጻነት የተጣሰበት ሹመት እየተሰጠ በመሆኑ የሚመለከተው አካል አካዳሚክ ነጻነት እንዲከበር ጣልቃ እንዲገባ ጠይቋል፡፡

ለማሳያነት አንድ መምህር አሥር ወር ያህል በውክልና ካገለገለ በኋላ በትምህርት ክፍሉ ምርጫ ከ27 መምህራን በ24 መምህራን ተመርጦ በድምር ውጤት 1ኛ ሆኖ ሳለ በሁለት መምህራን የተመረጠውን ግለሰብ የትምህርት ክፍል ኃላፊ አድርጎ መሾም የትምህርት ክፍሉን አካዳሚ ነጻነት ከመገፋት አልፎ ዩንቨርሰቲውን የአምባገነኖች ተቋም ያደርጋታልና የዩንቨርሲቲ ማህበረሰብና የሚመለከታቸው ሁሉ የአካዳሚክ ነጻነት ትግል እንዲትቀላቀሉ ጥሪ እናደርጋለን” በሚል ተወካዮቹ አሳስቧል፡፡

አድሱ አመራር በግልፀኝነት “ህግና ደንብ እንዲሁም እስኪሻሻሉ ድረስ ያሉትን የኃላፊነት አሰያየም መመሪያዎችን ተከትሎ እንዲሰሩ ካልተደርጉና በቀድሞ ከመጡበት ተቋም ወይም ተቋማዊ ትውውቅ መነሻ የሚደርግ ሹመት እንዲሁም በሁለም ዘርፍ የተቀዛቀዘው የዩንቨርስቲው ስራ እንቅስቃሴ በቅርብ ጊዜ ከበፊቶቹ የባሰ አምባገነነትን በዩንቨርሲቲው እንዲሚያሰፍን አካሄዳቸው ያሳያልና እንዲታረሙ እና ስህተቶቻቸውን በአስቸኳይ እንዲያርሙ እንዲደረግ እንጠይቃለን” ሲሉ የመምህራን ተወካዮቹ በላኩት ማስረጃና መረጃ አረጋግጦ ገልጿል።

አዲሶቹ ሀላፊዎች በህጋዊ አሰራር የካዳሚክ ነፃነት በማክበር የመማር ማስተማር ሂደት በማጎልበት የማህበረሰቡን ችግር ፈቺ በሆኑ ተግባር ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ በፖለቲካ አመለካከት በዝምታ የሚታለፍ ከሆነ ግን ተሹዋሚዎቹ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ታማኝነታቸውን ለማህበረሰቡ ሳይሆን አምጥተው ለሾሙዋቸው ካድሬዎች ስለሚሆን ምዝበራውም ሆነ ብልሹ አሰራር እንደሚቀጥልና ተቋሙን የበለጠ እንደሚጎዳ አስረድቷል።

የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ለትምህርት ሚኒስትር ያስተላለፈው ውሳኔ ከሶስት ወራት በፊት ገደማ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ከዋና ኦዲተር መ/ቤቶች የተውጣጣ የአመራሮችና የባለሙያዎች አጣሪ ኮሚቴ ከዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር ሰፊ የግምገማና የውይይት መድረክ ላይ “አብዛኞቹ በአስተዳደራዊ እርምጃ የሚስተካከሉ ሳይሆን ከፍተኛ የህግ ጥሰት የተፈፀመበት በመሆኑ በየዘርፉ የተፈፀሙ ጥሰቶች ላይ እርምጃ እንዲወሰድበት” በሚል በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲነሱ ተደርጎ በአዲሶቹ እንዲተካ ቢደረግም እስካሁን ህጋዊ ተጠያቂነት ሆነ የተዘረፈ ሀብት እንዲመለስ አለመደረጉን ከታማኝ ምንጮቻችን አረጋግጠናል። በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *