
ኢትዮጵያ ከዎላይታ ላሾ ከኬንያ ቀጥሎ ለታንዛኒያ የኤለክትሪክ ኃይል ለመሸጥ የተገባውን ስምምነት ተግባራዊ አደረገች።
በዎላይታ በሚገኘው ኡማ ወንዝ ላይ ከተገነባው ግቤ 3 ኤለክትሪክ ኃይል ማመንጫ ከሶዶ ላሾ የኃይል ማከማቻና ማከፋፈያ ማከፋፈያው በኬንያ እና በኢትዮጵያ መካከል ድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ሽግግር እያደረገ የሚገኘው በቅርቡ ታንዛኒያን በ400 ኪሎ ቮልት ኢሲንያ ማከፋፈያ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በኬኒያ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ዐቢይ አህመድ ወደ ታንዛኒያም እንደሚያቀኑ የሚጠበቅ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ወደ ኬኒያ የመጣው የኤለክትሪክ ኃይል ቀጥታ ወደ ታንዛኒያ እንዲሄድ የተገነባውን የኤለክትሪክ ማከፋፈያና ማከማቻ ጣቢያ ተመልክተዋል።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት እየሸፈነ የሚገኝው በዎላይታ ዞን በኡማ ወንዝ ላይ የተገነባው (ጊቤ_3 1887MW) ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ለአዲስአበባ ዋና ማከፋፈያና ለኬኒያ ቀጥታ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያስተላልፍ ዎላይታ ዞን ላሾ ቀበሌ የሚገኝ የኤሌክትሪክ የኃይል ቋት ማዕከል አሁን በተጨማሪ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገንዘብ የሚያስገኝ ኤለክትሪክ ሽያጭ ለታንዛኒያ ቀርቧል።



ከመላው ኢትዮጵያ አልፎ እስከ ጎረቤት ሀገራት ድረስ ብራሃን እየሰጠ ለራሱ ከመሬቱ ተፈናቅለው ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክት ያስገነባው ህዝብ እስከመቼ በጨለማ ይቆያል? በዓመት ከ40 ኢንዱስትሪ ፓርክ በላይ መገንባት የሚያስችል ገቢ የሚያስገኝ የፕሮጀክት ባለቤትና ጠባቂ የሆኑት ልጆቻቸው በየከተማው ጎዳና ላይ እየተሰቃዩ አንድ ኢንዱስትሪ ፓርክ እንኳን ስጠየቅ በዝምታ እስከመቼ ? ግድቡ ስጠናቀቅ ለዎላይታ ከ50MW በላይ ለመስጠት የተገባው ቃል ለምን ታጠፈ? የሚሉ ድምፆች ከፍ ብለው ይደመጣሉ።
በሀገሪቱ ከፍተኛ ኤለክትሪክ ኃይል ማመንጫ ዎላይታ ላሾ ፓውር ስቴሽን “በቀጥታም በዘዋዋሪም አከባቢውን ማህበረሰብ ረጅም ጊዜ ከቆዩ የጤና ጉዳት ይደርስባቸዋል” በሚል በተጠናው ጥናት መነሻ በማሰብ በዙሪያው ለሚገኙ ነዋሪዎች የካሳ ክፊያ የተወሰነ ቢሆኑም የዘረፉ ባለሙያዎች ከጉዳቱ አንፃር ለነዋሪዎቹ ከፍተኛ ትኩረትና ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ቢያሳስቡም ትኩረት ተነፍገዋል። በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ