በአንድ ሰፈርና ጥቅም ተጋሪዎች እየተመራ የሚገኘው የመላው ዎላይታ ህዝብ ማህበር ቀጣይ ሳምንት ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያካሂድ ተገለፀ።

የህዝብ ውግንና ባላቸው ግለሰቦች ተመስርተው የመላው ህዝብ ኩራት የነበረው የዎላይታ ልማት ማህበር 23ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ በመጭው ቅዳሜ መጋቢት 14/2016 ዓ.ም እንደሚያካሄድ ተነግሯል።

ልማት ማህበሩ በአዲስ መልክ ከተቋቋመበት ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ከመላው ዎላይታ ህዝብ፣ ከአባለት በሚሰበሰብ ሀብት፣ ከረጂ ድርጅቶች በሚያገኘው ድጋፍና ከገቢ ማስገኛ ተቋማት በሚሰበስበው ገቢ በዞኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ ያሳረፈው አሻራ እጅግ በጣም የሚደነቅና ለሌሎች አከባቢ ልማት ማህበራትም ተምሳሌት እየሆነ የመጣ በአጭር ጊዜ ተቋቁመው ውጤታማ የሆነ የሚሊዮኖች ሀብትና ኩራት ቢሆንም አሁን አሁን የፓለቲካ ማሽን የሌቦች ዋሻ በመሆን የተጀመረውን ዋና መስሪያቤት ህንፃ ግንባታ በሙስና በጅምር በማቆም ለሰራተኞቹ እንኳን ደሞዝ በጊዜ ለመክፈል እየተቸገረ ስለመሆኑ ማህበሩን በቅርበት የሚያውቅ ምንጭ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድቷል።

በአሁኑ ወቅት በማህበሩ ስር የሚመሩ በርካታ ዳሞታ ኮንስትራክሽን ጨምረው ያሉት በተዋቀረው በሌብነት፣ በአከባቢያዊና ጥቅም አደረጃጀት፣ በተሰራው ሴራ የአባላት ድጋፍና እምነት ማነስ፣ ከዚህ በፊት የሚሰሩ አጋር ድርጅቶች መቀነስ እንዲሁሂ ልምድና እውቀት ያላቸው ሰዎች ተገፍተው ከማህበሩ መልቀቅ ምክንያት እንደ ከ1970ዎቹ ጀምሮ እስከ 1993 ዓ.ም በማህበሩ የተደቀነው አይነት በአንድ ሰፈር ልጆች እንዲመራ ተደርጎ ህዝቡ “ማህበሩ የሁሉም አይደለም” በሚል ድጋፍ እንዲያቆም ድብቅ ሴራ በመኖሩ የመፍረስ አደጋ እንደተጋረጠበትም አክሎ ጠቁሟል።

“አንጋፋው የዎላይታ ልማት ማህበር በሰው ሀብት ልማት፣ በዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ፣ በትምህርት እና በተቀናጀ ጤና የትኩረት አቅጣጫ ዘርፎች በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች ከራሳቸው በላይ ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ በሚሰጡ ታታሪ አመራሮችና ሰራተኞች ተዋቅሮ የመላው ህዝብ ኩራት የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ያ አመራርና አብዛኞቹ ሰራተኞች እንዲወጡ በማድረግ እስከ ቦርድ ሰብሳቢ ድረስ በአንድ ሰፈር፣ ትውውቅና ጥቅም እንዲደራጅ በመደረጉ ልማት ማህበሩ የነበረውን ግርማ ሞጎስ እያጣ ነውና ብቸኛው የህዝብ ሀብት የሆነውን ለመታደግ ሁሉም ዎላይታ ያለልዩነት መረባረብ እንዳለበት” ጥሪ አቅርቧል።

ማህበሩ ከ1957 ዓ.ም ጀምሮ በዎላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ተሰማርቶ አያሌ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ከቆየ በኋላ ከ1970ዎቹ ጀምሮ እስከ 1993 ዓ.ም ባለው ጊዜ አሁን ላይ በማህበሩ የተደቀነው አይነት በአንድ ሰፈር ልጆች እንዲመራ ተደርጎ ህዝቡ ማህበሩ የሁሉም እንዳይልና ድጋፍ እንዲያቆም ድብቅ ሴራ በመኖሩ፣ ለልማት የሚሰበሰብ ገንዘብ ግለሰቦች ተከፋፍለው ስለበሉ እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች በማህበሩ ላይ ህዝቡ የእኔነት ስሜት እንዲያጠፋ በመደረጉ ተዘግቶና ተዳክሞ የቆየ ቢሆንም ያለልዩነት ከሁሉም አከባቢዎች የመላውን ህዝብ ጥቅም መነሻ ባደረገ መንገድ የተሰባሰቡ የህዝብ ልጆች በ1993 ዓ.ም ዳግም በአዲስ መልክ እንዲዋቀር በማድረግ ስራውን ጀምሮ በአጭር ጊዜ አስደማሚ ለውጦችን ማስመዝገቡን በርካቶች ይመሰክራሉ።

ባለቤትነቱ የመላው ህዝብ የሆነው ማህበሩ የዘንድሮውን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ከላይ የተዘረዘሩ ጥቂት ግለሰቦች የፈጠሩት ዘርፈብዙ ችግሮች ጫናና የመፍረስ አደጋ በተጋረጠበት በዚሁ ወቅት ለ23ኛ ጊዜ ከፌደራል ጀምሮ በተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች ያሉ የልማት ማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች፣ ከልማት ማህበሩ ጋር የሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ተወካዮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በቀጣዩ ቅዳሜ 14 መጋቢት 2016 ዓ.ም በዎላይታ ሶዶ ከተማ ጉተራ አዳራሽ እንደሚያካሂድ ከስፍራው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *