መድረኩ የአመራሩን የፖለቲካ መበስበስ በተጨባጭ ያጋለጠ ታሪካዊ ቀን መሆኑን የዎላይታ ዞን የመንግስት ሰራተኞች የብልጽግና ፓርቲ አባላት ተናገሩ።

በዎላይታ ዞን ፐብሊክ ሰርቫንት የብልፅግና አባላት ኮንፈረንስ ላይ አባሉ በዘጠኝ መሠረታዊ ድርጅቶች ኮንፈራንስ በዛሬው ዕለት ያካሄደ ሲሆን “የአባሉ ትግል ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ወደ ላቀ ከፍታ የተሸጋገረበት ሆኖ ታይቷል” ሲሉም አባላቱ ገልጿል።

በአበልጅ (ጃላ) እና በአከባቢ፤ በሌብነት፤ በጎሳ፤ በጥቅም ላይ የተሳሰረ የስልጣን ኮሪቻ መፍረስ አንደምገባው አባሉ በሁሉም መሠረታዊ ፓርቲዎች በምሬት ያነሳ ሲሆን በዎላይታ ዞን መንግስት ሰራተኞች፣ መምህራን፣ ሶዶ ከተማ፣ አረካ ከተማ፣ ቦዲቲ ከተማ፣ ዳሞት ወይዴ ወረዳ፣ ድጉና ፈንጎ ወረዳ፣ ሁምቦ ከተማ፣ ገሱባ ከተማ፣ ጉኑኖ ከተማ፣ ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ በሁሉም መሠረታዊ ፓርቲዎች ላይ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ከየአካባቢው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ደርሷል።

አመራሩ አንዱ የአንዱን ልጅ አይን በመያዝ በአበልጅነት ወደ አመራር ፑል በኔትወርክ በመሳሳብ ሌብነታቸውንና የቆሸሸ ተግባራቸው እንዳይጋለጥ እንደ ቃል መገባቢያ መንገድ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ በዛሬው ዕለት በርካታ መድረኮች ላይ በአባላቱ የተነሳ ቁልፍ ጉዳይ ስለመሆኑ ተገልጿል።

አረካ ከተማ የሚገኘው ቼንትሮ አዩቲ ፔር ለኢትዮጵያ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በተስፋዬ ይገዙና በአበልጆቹ አማካይነት የተቋሙ የቀድሞ ህጋዊ ሳይት ፕላን እንዲመክን ተደርጎ በግለሰብ ስም አዘጋጅተው ማስተላለፋቸው በተጨባጭ በአባላቱ ከተነሱ ዋና ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ ተገልጿል።

በዎላይታ ሶዶ ከተማ ሄሎ ሞተርስ መኪና መገጣጠሚያ የኢንቨስትመንት ቦታ ከግለሰቦች ገንዘብ ተቀብሎ ከስታንዳርድ ውጪ 100,000 ካሬ መሰጠቱን፤ የሶዶ ከተማ መርካቶ ገበያ ግንባታ በሚሊዮን ገንዘቦች መመዝበሩ፤ በሶዶ ከተማ አስተዳደር ላይ ቀዳማዊት እመቤት ያስገነባችው የዳቦ ፋብሪካ ላይ በከፍተኛ ገንዘብ ተገዝቶ የቀረበ የስንዴ ዱቄትን በአመራር ውሳኔ በሙሉ በመሸጥ ስርቆት መፈጸማቸው በተለያዩ መድረኮች በአባላቱ ተነስቷል።

የወይቦ መስኖ ግንባታ ላይ በካሳ ሰበብ የሙስና ወንጀል መፈጸማቸው፣ የህዝብ ተቋም የሆኑት ወልማ እና የወላይታ ቴሌቪዢን ተቋሞችን ሃብት እየመዘበሩ መሆናቸው፤ ቅጥር፣ ዝውውር፣ ደረጃ ዕድገትና ሹመት በኔትወርክ አደረጃጀት ማካሄድ፣ አመራሩ የአበልና የነዳጅ አጠቃቀም የፋይናንስ ደንብና አሰራር አለመከተሉ፣ በመላ መዋቅር የሚገኘው አመራር በመሬት ወረራና በሌላ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር መዘፈቁ እና ሌሎችንም የአመራሩን ብልሽት አባላቱ ያለምንም ፍርሃት በአደባባይ በማስጣት ከፍተኛ ትግል አካሂደዋል።

የአባሉ ትግል ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ለአብነት ያክል የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መስፍን ዳዊት በመሩት መድረክ አባላቱ በሐቅ ላይ ተመስርተው እየተናገሩ አልንበርከክ ስላሉት በመጮህ እያለቀሰ ብንሞትም ስልጣን አንለቅም እያንዳንድሽን ልክ እናስገባለን” በሚል በመዛት በድንጋጤ አዙሮት ጠረጴዛ ላይ አንገቱን ደፍቶ ሲያለቅስ የታየ ሲሆን በሌላ መድረክ በተለይ የዞኑ ኢንተርፕራይዞች ባለበት መድረክ ላይ አንድ ከአመራሩ የጥቅም ግንኙነት የፈጠረ መንግስት ሰራተኛው ሕሊናውን አቆሺሾ ሲያወራ ተሰምቷል።

እንደ መረጃ ምንጮቻችን ገለፃ በኮንፈረንሱ ቀድሞው ለህዝቡም ለፓርቲውም እኩይ አላማውና ድርጊቱ ገሃድ የወጣበት የኔትወርክ ቡድኑ በተለይ የመንግስት ሰራተኛውን በአበልና በጥቅማጥቅም ዝም ለማሰኘት የተደረገ ሙከራ በርካታ ቦታዎች ላይ የከሸፈ ሲሆን አባላቱ በግልጽ ቋንቋ በዞኑ እየሆነ ያለው “በመንግስት ላይ እምነት ለመጣል እንኳን የሚያስቸግር ነውና እውነትም የብልፅግና ፓርቲያችን ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥና የራሱ ፓርቲ ስም ጭምር የሚያጎድፍ እነዚህ ቡድኖች በዘረጉት የማይመጥን የግለሰቦች ኔትወርክ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ እርምት እርምጃ እንዲወስድ” የሚል ሀሳብም በሁሉም አከባቢዎች ያለልዩነት ማለት በሚቻል ደረጃ ተንፀባርቋል።

በአጠቃላይ ዎላይታ በአንድ ሰዉ እጅ መዳፍ በወደቀበት ሁኔታ በአከባቢው ብልጽግናን ለማረጋገጥና ሕዝቡን ማሻገር አስቸጋሪ ነውና ይህ ትግል የዎላይታ ህልውና ላይ የሚደረግ ትግል ስለሆነ እኔ ዎላይታ ነኝ የሚል ሁሉ ተጨባጭ እውነትን መሠረት በማድረግ የሌቦች ቡድንን በፅናት መታገል እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።

በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *