ሀሰተኛ የገቢ ደረሰኝ በማዘጋጀት የመንግስት ቀበሌ ቤትን እየሸጡ የተያዙ ግለሰቦች በአመራር ትዕዛዝ እንዳይከሰሱ መደረጉም አነጋጋሪ ሆኗል።

የአቶ አሰፋ አድማሱ የተባለ ግለሰብ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ድል በገሬራ በተባለ ቀበሌ ለመንግስት ቤት ኪራይ የከፈለበት (0538901) ንምራ ቁጥር ያለው ሕጋዊ ደረሰኝ ተጠቅሞ አቶ ተስፋሁን በለጠ ( የአማራር ወንድም ) የተባለ ግለሰብ ከላይ ከተጠቀሰው ጋር ተመሳሳይ ንምራ ቁጥር (0538901) ያለው የሕገወጥ ደረሰኝ አመሳስሎ በማሳተም የቤት ሽያጭ ውል ማጽደቂያ በአራዳ ገቢዎች የተከፈለ በማስመሰል የመንግስት ቀበሌ ቤት ለመሸጥ የሰራው ሀሰተኛ ደረሰኝ ስለመሆኑ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጥ ችሏል።

ሀሰተኛ ደረሰኝ በማተም የተፈጸመው ወንጀል ሳያንስ ንብረትነቱ የመንግስት የሆነውን የቀበሌ ቤት ለግለሰቦች ለመሸጥ ሲሞክር የተያዘው ግለሰብ በዎላይታ ዞን ውስጥ አንድ የዞን መምሪያ ኃላፊ ወንድሞ መሆኑ የተፈጸመውን ወንጀሉ አሳሳቢ ከማድረጉም በላይ ወንጀለኛው በሕግህም ተጠያቂ እንዳይሆን ማድረጉም በመረጃው ተገልጿል።

የዞን አቃቤ ሕግ ሙሉ መረጃ ደርሶበት ክስ ከመሰረተ በኃላ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ መጥሪያ ወጥቶለት ተጠርጣሪው በሶዶ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት እየሰራ ባለበት አሁን ያለው የዞን አመራሮችና የሶዶ ከተማ አስተባባሪዎች ጭምር ተሳስቦ የተነጋገሩ ቢሆንም “ጉዳዩ ይፋ ከወጣ በዘርፉ የተፈፀሙ በርካታ ጥፋቶች ይጋለጣሉ” በሚል በመፍራት ግለሰቡ ወደ ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ መደረጉንም ከምንጮቻችን አረጋግጠናል።

በዚህ መንገድ ሕገወጥ ደረሰኝ ሕትመት እንዲሁም የቀበሌ ቤት ለግለሰቦች ለመሸጥ በአደባባይ የሞከሩት ቢያዙም በአመራር ሽፋን እየተሰጠ ወንጀል ፈጻሚው በሕግ አለመጠየቁ በአከባቢው የህግ የበላይነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት እንደሆነ አጠያያቂ እንደማይሆን ይገለጻል።

በዎላይታ ዞን ይሁን በክልል ያሉ የፍትህ ተቋማት ይህንንና መሰል ወንጀለኞችን ተከታትሎ ወደ ሕግ እንዲያቀርብ እየጠየቅን ይህ ሳይሆን ስቅርና ለሚፈጸመው ወንጀል የመንግስት አመራር ሽፋን እየሰጠ የሚቀጥል ከሆነ ስርዓት አልበኝነት ይነግሳል” በሚል በርካቶች ይጠይቃሉ።

ዎላይታ ዞን በክልሉ ከፍተኛ ግብር የሚሰበሰብና የመሰብሰብ አቅም ያለው ቢሆንም አመራሮች ከጥቂት ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር ሀሰተኛ ደረሰኝ ጭምር እንዲዘጋጅ እያሳተሙ በወንጀል ተግባር ስለመሰማራታቸው ተጨባጭ መረጃዎች የደረሰን ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ከህብረተሰቡ የሚሰበሰብ ገንዘብ በተለያዩ መንገዶች የሚመዘበር በመሆኑ ለአከባቢው ልማት ሆነ ለመንግሥት ሰራተኞችም ደመወዝ በግዜ መክፈል እንዳቃታቸው ተደርሶበታል።

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *