“በአሰራር ጉድለት ምክንያት ደሞዝ እየተከፈለን አይደለም፤ ተቆራርጦ የሚገባ ደሞዝም በፈረቃ እየቀረብን ነው” በሚል የዎላይታ ዞን የመንግሥት ሰራተኞች ቅሬታ አሰሙ።

የደሞዝ ክፍያው መዘግየት በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ተፅኖ እንዳሳደረባቸው የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ በአብዘኛዉ መዋቅሮች ደመወዝ በጊዜ ባለመከፈሉ በዝህ የኑሮ ዉድነት የቤት ክራይ፤ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ እንዲሁም የቤተሰብ ቀለብ መግዣ በማጣት ለከፋ ጉዳት ከመድረሳቸዉ አስቀድመዉ ምላሽ እንዲሰጥበት” ሲሉም አክለው ጠይቀዋል።

“ደመወዝ የሚሰጥበት ወር ገደብ ቢያልፍም እስከዛሬ ድረስ የመንግስት ሠራተኛ ደመውዝ ተከፍለው እንኳን ኑሮ ውድነትን መቋቋም ባልቻለበት ወቅት ደመውዝ ተከልክለን በዝምድና፣ ከሰፈር፣ በጋብቻ እና በአይን አባትነት ትስስር የተዋቀረው የአከባቢው አመራር ቡድን በየቦታው ድግስ በማውጣትና በሙስና ተግባር ተጠምደው እኛ ተረስተናል” ሲሉ በተለያዩ መዋቅር እየሰሩ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ተመሳሳይ ቅሬታ አቅርበዋል።

በዞኑ ከሚገኙ 22 መዋቅሮች ማለትም 16 ወረዳዎች፣ 5 የከተማ አስተዳደር እና ከዞን መዋቅር የመንግስት ሰራተኞች የየካቲት ወር ደመውዝ በፈረቃ ተደርጎ የተከፈላቸው 3 ብቻ ስለመሆኑና የተለያዩ መዋቅሮች የስራ ማቆምና ለተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣት ዘመቻ ለመጀመር እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የዞኑ መንግስት በዞኑ የተፈፀሙ ህገወጥ ቅጥሮችና የማዳበሪያ ዕዳ ይህንን ችግር ማስከተሉን በመግለፅ ሰራተኛ ሳይሆኑ ደሞዝ የሚከፈላቸው ጭምር መኖራቸው ተረጋግጦ ለማስተካከልና የደሞዝ ችግሮችንም ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው” በሚል አንድ የዞኑ መንግስት ከፍተኛ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ምላሽ የሰጠ ቢሆንም ዎላይታ ዞን በክልሉ ከፍተኛ ግብር የሚሰበሰብና የመሰብሰብ አቅም ያለው ቢሆንም በተቃራኒው ደግሞ ከህብረተሰቡ የሚሰበሰብ ገንዘብ በተለያዩ መንገዶች የሚመዘበር በመሆኑ ለአከባቢው ልማት ሆነ ለመንግሥት ሰራተኞችም ደመወዝ ሆነ ወደ መስክ የወጡበት ወጪ በግዜ መክፈል አለመቻሉ በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ እየፈጠረ ስለመሆኑም ተገልጿል።

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *