ሊስቶሮ እየሰራ እስከ ሁለተኛ ድግሪ የተማረው ወጣት ከህይወት ተመክሮ መፅሀፍ እየፃፈ ነው

“ሰላም እንዴት ናችሁ ? እኔ ወጣት አማኑኤል ዮሴፍ እባላለሁ። በዎላይታ ነው የተወለድኩት። የሚደግፍ አጥቼ ከትምህርት ሰዓት ውጪ ሊስትሮ በመጥረግ ጫኝና አውራጅ በመሆን ፓርክንግን ጨምሮ እየሰራው ማታ ማታ እያነበብኩ የመጀመሪያ ዲግሪዬን በወልቂጤ ዩንቨርስቲ 2011 ላይ ጨረስኩኝ። ከዛ በኋላ 2012 ሥራ ገባው፣ ወዲያው በዎላይታ በአንድ ወረዳ በኃላፊነት ደረጃ አገለገልኩ።

ሁለተኛ ዲግሪዬን በዋቸሞ ዩንቨርስቲ በChemical Engineering እየተከታተልኩ በተለያዬ ሥራ መስክ መንቀሳቀስ ዳጌት ሆኖ አላንገላታኝም፤ በ2015 ዓ.ም በክብር ተመረቅሁ፣ ችግሮቼን ፊት ለፊት እየተጋፈጥኩኝ በአሸናፊነትና በድል እየተጓዝኩ እገኛለሁ።

በአሁኑ ወቅት “ታላቁ ሀብት” ( Bayra Duretettay ) በተሰኘ ርዕስ ከልጅነቴ ጀምሮ ያሳናዳሁትን ሁለገብ የግጥም መጽሐፍ በአማርኛና በዎላይታቶ የጀመርኩትን የጽሑፍ ሥራ በማገባደድ ላይ እገኛለሁ። ይህን መጽሐፍ ለማሳተም በተለያዬ መንገድ ለመንቀሳቀስ ሞክርያለሁ።

በእነዚያ ሁሉ ለመናገር በሚከብዱ ችግሮች ወቅት ፈገግታ እንኳን ከፊቴ ሳይለየኝ ሊስትሮ በመጥረግ ጫኝና አውራጅ በመሆን ፓርክንግን ጨምሮ ማታ ማታ የጥናትና ምርምር ሥራዬን እየሰራሁ ቀን ቀን በጠቀስኳቸው ሥራዎች ላይ ባለመታከት ተሰማሪችያለሁ። በዚህ ውጣወረድ ሁሉ በይዘቱ ለየት ያለ የህይወት ተመክሮ ጨምሮ በመጽሐፉ መንፈሳዊ፣ ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ለየትኛውም አንባቢ እንደሚኾን ተስፋ የማደርገውን እየጨረስኩ እገኛለሁ።”

ማስታወሻ ፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የባለታሪኩን ተመክሮ ቀጥታ ያቀረበው “ለበርካቶች አስቸጋሪውን የህይወት ውጣውረድ አልፎ ስኬታማ እንዴት መሆን ይቻላል?” ለሚሉት ሊያስተምርና መልካም ተመክሮ ሊሆን ይችላል በሚል መነሻ እንዲሁም በመሠል ሁኔታ ውስጥ እያለፉ የሚገኙትን ለማበረታት ያቀረበ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትም ለእንደዚህ አይነት ብርቱ ወጣቶች አላማ እውን እንዲሆን ድጋፍ ቢያደርጉ መልካም ነው እንላለን። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *