ከዎላይታ ጦና ቦክስ ክለብ እስከ ኢትዮጵያ ኩራት 👐 68ቱም ወርቅ ነው!!

ኢትዮጵያዊቷ ድንቅ ቦክሰኛ ቤተል ወልዴ፥ በ66 ኪ.ግ ከሞዛምቢኳ ቦክሰኛዋ ጋር ለፍፃሜ ተገናኝታ በሚገርም ብቃት 5 ለምንም በጋና አክራ ከተማ በተካሄደው በዘንድሮው የመላው አፍሪካ ጨዋታ፥ ለኢትዮጵያ 2ኛ የሆነ የወርቅ ሜዳልያ በማስመዝገብና ለራሷ ደግም የወርቅ ሜዳልያ ቁጥር ከፍ በማድረግ ስሟን በደማቁ የታሪክ ማህደር መሰነድ ችላለች።

ከዎላይታ-ኢትዮጵያ እስከ አለምአቀፍ ቦክስ ስፓርት ውድድር ከ67 በላይ ወርቅ ተሸላሚ እንዲሁም ለአራት ዙር የቤልት ውድድር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቦክሰኛ ሻምፒዮና የሆነችው ቤቴል ወልዴ 68ኛውን የወርቅ መዳሊያ በመላው አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድር በማግኘት አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ መቀጠሏን በአደባባይ አረጋግጣለች።

ቤተል ወልዴ ውልደትና ዕድገቷ ዎላይታ ሶዶ ነው፥ በቦክስ ስፓርት የተመሰከረላት ወጣት ናት፣ አብዛኞቹን ተጋጣሚዎችን በበቃኝ ማሸነፏ ደግሞ ለየት ያደርጋታል፤ እስከአሁን ድረስ ባደረገችው በቦክስ፣ በኪክ ቦክስና ሞይንታይ ውድድሮች አሸናፊ በመሆን የ67 ሜዳሊያዎች ባለቤት ናት። ለየት የሚያደርገው ደግሞ ከእነዚህ ሜዳሊያዎች አንዱ ብቻ የነሀስ ሲሆን ሌሎች በሙሉ የወርቅ ብቻ መሆኑንም ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ማረጋገጧ ይታወሳል።

መነሻውን የጦና ቦክስ ቡድን ያደረገችሁ ይህቺ ብርቷ ሴት ከዓመታት በፊት ዎላይታ ዞንን ወክላ በክልልና በአገርአቀፍ ደረጃ በሴቶች ቦክስ ስፖርት ሻምፒዮን በመሆን ትታወቃለች።

ቀጥሎ ባሉ ጊዜያት ለአካዳሚ፣ ለኒያላና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ክለብ በመጫወትም በርካቶችን በበላይነት በማሸነፍ እንዲሁም የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆን እውቅና ያተረፈች እንቁ ወጣት ናት።

በቅርቡ መስከረም ወር 2015 ዓ.ም ኢትዮጵያን ወክላ በተሳተፈችበት የሞይንታይ ኢንተርናሽናል ውድድር የቤላሩሱዋን ተወዳዳሪ በበላይነት አሸንፋ የሀገሯን ስም ከፍ አድርጋ አስጠርታለች።

በጋና አክራ በተካሄደው 13ኛ መላው የአፍሪካ ጨዋታ ላይ ኢትዮጲያ በቦክስ ውድድር ከ37 ዓመት በኋላ አዲስ ታሪክ ለሀገራቸው የወርቅ ሜዳሊያ ካሸነፈችሁ ከሌላኛዋ ብርቱ ቦክሰኛ ቤቴሌሄም ገዛሃኝ አሁን በሚያሳዩት አስደናቂ አቋም ቀጣይ በአለምአቀፉ መድረክ ለኦሎምፒክ በማለፍ የመጀመሪያዋ ሴት ቦክሰኛ ይሆናሉ በሚል በርካቶች ይመሰክራሉ።

ላለፋት አምስት ቀናት በጋና አክራ ሲካሄድ የቆየው 13ኛው የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድር ከ50 የአፍሪካ ሀገሮች ከ640 በላይ አትሌቶች መሳተፋቸው የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያ በ47 ወንድ፣ በ40 ሴት በድምሩ በ87 አትሌቶች የተወከለች ሲሆን 7 የወርቅ፣ 7 የብር እና 4 የነሐስ በድምሩ 18 ሜዳልያዎችን ማስመዝገብ ናይጄሪያን ተከትላ በሁለተኛነት ማጠናቀቋን ከአፍሪካ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *