በግብፅ በሚካሄደው በዘንድሮው የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ዎላይታ ዲቻ እንደሚሳተፍ ተገለፀ።

በግብጽ ካይሮ በሚካሄደው የ2024 የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ላይ በወንዶች በዎላይታ ድቻ እና ሙገር ሲሚንቶ ሀገራችን ኢትዮጵያ ትወከላለች።

በትናንትናው ዕለትም የመመዝገቢያ ክፍያ እና ተያያዥ ጉዳዮችን አጠናቀው የመጨረሻ ምዝገባ አካሂደው በአዘጋጁ አካል ማረጋገጫ ማገኘቱ ተገልጿል።

በቀጣይ ቀናትም ቀሪ ዝግጅቶችን አጠናቀው ከሚያዚያ 12-24/2024 በሚካሄደው ሻምፒዮና ላይ ይሳተፋሉ።

በሴቶች ብቸኛ የሀገራችን ተወካይ ብሄራዊ አልኮል ክለብ ሲሆን ክለቡም ዝግጅቱን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ውድድሩም ከሚያዚያ 24- 5 ግንቦት/2024 በግብጽ ካይሮ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ያወጣው መረጃ ያመለክታል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *