ዎላይታ ሶዶ ከተማ
በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሀሰተኛ ሰነድ የታገዘ የመሬት ወረራ እየተስተዋለ ነው ተባለ
ለWT በተለያዩ መንገዶች እየደረሰ የሚገኘው መረጃ እና ማስረጃ እንደሚያመለክተው በዎላይታ ሶዶ ከተማ አንዳንድ ግለሰቦች በህገወጥ መንገድ ህጋዊ ውሳኔዎችን ሆን ብሎ ለማዛባት እና ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የይዞታ ቦታ፣ የማስፋፊያ መሬት ለማግኘት እና ሌሎች ተያያዥ ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ጭምር መሳተፋቸውን የሚያሳዩ ሰነዶች በመድረስ ላይ ይገኛል።
በዚሁ ህገወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉ ሰዎች መረጃዎችን ለግዜው በስም ጠቅሰን መረጃውን ካደረሰን የተጀመሩ ህጋዊ የምርመራ ሂደትን ልያዛባ ስለሚችል ለግዜው ያቆየን በመሆኑ ወደፊት WT ተጨማሪ የምርምራ ዘገባ ለተከታዮቹ እስከሚያደርስ በየትኛውም መንገድ የሚመጡ መረጃችንና ማስረጃዎችን ጉዳይ ለሚመለከታቸው አካላት በማድረስ ላይ መሆኑንም እንገልፃለን።
በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማስረጃ አለኝ የሚል ማነኛውም ግለሰብ በውስጥ መስመር ሆነ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ጥቆማ በመስጠት ህገወጥ ተግባርን በመከላከል ህጋዊ አሰራር በአከባቢው እንዲሰፍን የዜግነት ግዴታ እንዲወጡ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።