
በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ 14ኛ ዙር ጨዋታ ወደ ባህርዳር ከተማ አቅንተው ሀዲያ ሆስኦና አቻውን የገጠሙት የጦና ንቦች ከሜዳ ውጭ ዛሬም በተደጋጋሚ ድል ቀንቷቸዋል።
በጨዋታው የጦና ንቦች በሁለተኛ አጋማሽ ቸርነት ጉግሳ እና ፀጋዬ ብርሃኑ የማሸነፊያ ጎል ያስቆጠሩ ሲሆን በዚሁም 17 ነጥብ ይዞ የደረጃ ለውጥ አድርጓል።
ዎላይታ ዲቻ በተላይም በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ አከባቢ የውጤት ቀውስ ውሰጥ በመግባቱ ከደጋፊዎች ብርቱ ተቃወሞ በመነሳቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥቶ የተለያዩ ማስተካከያ እርምጃዎችን በመውሰዳቸው ጥሩ የውጤት መሻሻል እያሳዩ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
FT Wolaita Dicha 2_0 Hadiya Hosana