FactCheckingNews

የጦና ብርጌድ በፋኖ አደረጃጀት ምን አለው⁉️

በሰሞኑን መንግስት በመንግሥት ሚዲያዎች <የከሸፈው ሴራ> በሚል አንድ ከታች በምስል የሚታይ ወጣት ይታያል። በንግግሩ ባሳለፍነዉ ጊዜ የዎላይታ ህዝብ ራስን በራስ ማስተዳደር እንዲችል በተደረገው ሰላማዊ ትግል ወቅት የሌለና የማይታወቅ ሰው “የዎላይታ ነፃነት ግንባር” ብለዉ ከአሸባሪዎች ጋር አብሮ እንደሚሰራ ሲናገር ይደመጣል። ብዙዎች ግለሰቡን “የዎላይታ ተወላጅ ወይም የካምባታ ተወላጅ” ነዉ ሲሉም ተሰምቷል። ግለሰቡ ከዚህ ቀደም የዎላይታ ፖለቲካ ተሳትፎ ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታወቅም አይደለም።

በእርግጥ የዎላይታ ሕዝብ ጨንቃ ላይ የተጠመደውን ጭቆና ለመስበር ዘላቂ ማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ…. ወዘተ ለመመለስ የትጥቅ ትግል እንደ አንድ አማራጭ በማድረግ ሳይሆን ባሳለፍነው ሶስት አስርተ አመታት በሰለጠነ መንገድ እጂግ ለሌሎች ተምሳሌት በሚሆን አኳኋን ሰላማዊ ትግል ሲያካሂድ መቆየቱ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ መሆኑ ይታወቃል።

የዚህ ዶክመንተሪ ህልውና ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባና ለዎላይታ ጥላቻ ያለው ሁሉ እየተነሳ ስለዎላይታ ያልሆነ ነገር ቢያወራ “እውነት ነው” ማለት ነው? በሚል በርካቶች ቅሬታ ያቀርባሉ ይተቻሉም።

በምስሉ ላይ ከታች የሚታየው ግለሰብ ከገባበት ሱስ ጋር በተያያዘ በጣም ተጎሳቁሎ፣ ከስቶና ጦቁሮ፣ ለመለየት እስከሚያደግት ድረስ ከሰውነት ተራ ወጥቶ ይታያል። ዶክመንተሪውን ካያችሁት አንድ ቦታ ላይ ይመጣና … “የጦና ብርጌድ በፋኖ አደረጃጀት የሚባል አለ”…. ምናምን ይልና፤ ምንም አይነት ሌላ ዝርዝር ነገር ሳያወራ አንድ ጊዜ ብቻ ታይቶ ይጠፋል።

በዶክመንተሪው የግለሰቡ ስም “አንዷለም ታደሰ” ተብሎ የሚጠራ ልጅ በትክክለኛ ስሙ “አቤኔዘር ኢሺኖ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፤ በዎላይታ የኖረ የከንባታ ተወላጅ ነው። ዎላይታ ተወልዶ አድጎ በኖረባቸው ጊዚያቶችና በኋላ ላይ ከሀደሮ እየተመላለሰ በዎላይታ በሚሰራቸው ወንጀሎች የተነሳ በህግ ስለሚፈለግ ከዎላይታ ወጥቶ ከጠፋ እረጅም አመታትን እንዳስቆጠረ ግለሰቡን በቅርበት የሚያውቁ ይመሰክራሉ።

ዎላይታ አገር ያቆማል እንጅ አገር አይበትንም። ዎላይታ ወደ ኢትዮጵያ ከተቀላቀለ ጀምሮ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንዲከበርለትን ሀበገሪቱ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እንዲሰፍ በየደረጃው ሰላማዊ ትግል ከማድረግ ውጪ በምንም አይነት ሁኔታ ላይ የራሱ የሆነ ሌላ አላማ አንግበው ከተነሳው አማፅያን ጋር ተባብረዉና ተለጥፎበት በአገር ላይ የተነሳበት ወቅት አለመኖሩን ታሪክ ያስረዳል።

ሀገርንና ሕዝብን ያከብራል ተከባብሮ እና ተግባብቶ ከሊስትሮ እስከ አገር መምራት የበቁ ለአገር ታማኝ ሆነዉ፤ የፖለቲካ መዋቅሩ፤ እና በየዘመኑ የምመጡ መሪዎች በሚያነሱት በእርስ በራስ ግጭትና ጦርነት እየተሳተፉ ለሀገራቸው መስዋዕትነት እየከፈለ እዚህ ደርሰዋል እንጅ ዎላይታ ከአማጽያን ጋር አያብረው አያውቅም።

በመሆኑም በዶክመንተሪው የተገለጸው ግለሰብም፤ የተገለጸው ፓለቲካ ፓርቲ ተሳትፎ የሌለውና በአከባቢው የማይታወቅ ስለመሆኑም ከተለያዩ ግለሰቦች ያገኘነው ተጨማሪ መረጃ ያረጋገጥን ሲሆን በዎላይታ አከባቢ ከዚህ በፊት ከህዝቡ ጋር በምንም አይነት የድንበር ሆነ የህዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች አንፃር የማይገናኝ ፓለቲካ ድርጅቶችና ቡድኖች እንቅስቃሴ ጋር “ግንኙነት አላቸው፤ ይደገፋሉ” በሚል ምንም ባልተረጋገጠበት መረጃ ግለሰቦችን የማሰር፣ ከስልጣን የማስወገድ፣ ሰብዓዊ መብት የመጣስ፣ እንዲሰደዱ እንዲሁም አንዳንዶቹ ያንን ክስተት ደግሞ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የቅም በቀል መወጣጫ እንዲሆን የተደረገበት ህገወጥ ዘመቻ ዳግም እንዳይከሰት የሚመለከተው አካል ተገቢውን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ጥሪ እናቀርባለን።

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *