“በቅድሚያ ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል ለህዝብ አንድነት ፀር የሆኑ ቡድኖች ተወግደው ለህዝብ ክብርና ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጡት የሚበዙበት የፍቅርና የሰላም እንዲሆን እየተመኘን ወደ አንገብጋቢውና አስቸኮይ መልዕክት ቀጥታ እንሻገራለን።

የዎላይታ ህዝብ ከታሪኩ የምማር ኩሩ እና ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር በፍቅር ተቻችሎ የሚኖር ህዝብ እነደሆነ በተጨባጭ የሚታወቅ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የዎላይታ ህዝብ በርካታ የፖለቲካ ምዕራፎችን በተለያዩ መንግሥታት እና ሥርዓቶች ጊዜ ማሳለፉ የሚታወስ ነው።

በእነዚያ መንግሥታዊ ሥርዓቶች ያሳለፍናቸው ሀቆች እንደተጠበቁ ሆኖ በቅርቡ በ2/3 ዓመታት በዎላይታ ውስጥ በተፈጠረው በአበልጅ ሥርወ-መንግስት፣ በጎሳ፣ በሰፈር አደረጃጄቶች የዎላይታ ከተሞች ላይ በተለይም በዎላይታ ሶዶ ከተማ፤ በአረካ ከተማ እና ለሎች ከተሞች ላይ መሬት በተደራጀ ሁኔታ በአመራር እየተመራ እና ማንኛውም ሌብነት እና ዝርፊያ በስልክ ትዕዛዝ ብቻ የሚመራ ስሆን ዋና ካፒቴኑም አቶ ተስፋዬ ይገዙ መሆኑ በራሱ በብልጽግና ፓርቲ አጣሪ ኮሚቴ መረጋገጡ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡

ህገ-ወጥ ቡድን ከዎላይታ አብራክ ወጥተው የዎላይታ ህዝብን በመዝረፍ፣ በመሥረቅ እና በዎላይታ ህዝብ ላይ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳት እያደረሰ መቆየቱን ብልጽግና ፓርቲም በመረዳት ላደረገው የማጣራትና የመለየት ሥራ ህዝቡ ከፍ ያለ ምስጋና ያለው ብሆንም ሰሞኑን የብልጽግና መንግሥት እና ፖርቲ አቶ ተስፋዬ ይገዙ የፓርቲው ሥራ-አስፈጻሚ ከመሆኑ ጋር እና የእርሱን የለበጣ/የውሸት ይቅርታ ጥያቄ አያይዞ የእሱን እገዳ ለፓርቲው አሰራር ጤንነት” በሚል ሰበብ “እገዳው እንዲነሳመባሉ የህዝቡን ከፍተኛ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ጉዳቶችን ከምንም ሳይቆጠር ችላ ያለ ውሳኔ እንደሆነ ያመላክታል፡፡

አቶ ተስፋዬ ይገዙ ይህን ችግሩን “ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ አይለምደኝም” በሚል የበቀል እና ክፋት መንፈሱን ደብቆ ይቅርታ ልጠይቅ ይችላል ነገር ግን ሰርቆ ካሰረቀ በኋላ፤ ካወደመ በኋላ፤ ከቀጠፈ በኋላ፤ ከቃጠለ በኋላ፤ ግጭትና ሞትን በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ከመራ በኋላ፤ ከ”Excellency Center” በኋላ የምን እርቅ ነው? በፓርቲ ዲሲኘልን ከመዳኘት በስተቀር? ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትመራው ብልጽግና የመሰለ በትልቅ ፖርቲ በከፍተኛ ዲስፕሊን እና ቆራጥነት እየተመራ ያለ ስሆን እንድህ ዓይነት ተራ ስግብግብ ነጣቂ የራሱ ሥራ-አስፈጻሚ አባል አድርጎ ለማስቀጠል ከታሰበም ጭምር ልጠንበት የሚገባ ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ የብልፅግና ፖርቲ የአንድ ሥራ አስፈፃሚ አባል ሌብነትን ለመሸፋፈን የሚያደርገው ጥረት የሚመስል ውሳኔ ከብልጽግና እንዴ ፓርቲ ይኖራል ግምትና ሀሳብ ባይኖርም በግለሰብ ደረጃ ደግሞ የሚገለጽ አስተሳሰቦች ይጠፋሉ ተብሎ አይገመትም፡፡ ምክንያቱም ከፍተኛ የገንዘብ ክምችት የፈጠረ አስፈሪ ቡድን ስለተገነባ እና በቅርቡ ይህ ቡድን የተለያዩ ግለሰቦችን ለመያዝ ተብሎ እስከ 30 ሚሊዮን ብር ድረስ ተሰብስቦ እንደነበረ ስለሚታወቅ፡፡

እነዚህ የዎላይታ ጠላት የሆኑት የአበልጅ ዳይናሲቲ መሪ እና አባላት ከህዝባችን ተወግዶ ማየት የመላው የዎላይታ ህዝብ ከፍተኛ ፍላጎት ስሆን ብልጽግናም ይህን ክፉ አመኬላ ከህዝባችንና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማስወገድ አማራጭ የሌለው መሆኑን እንደሚረዳ ምንም ጥርጥር የለለው ብሆንም ብልጽግና ለዎላይታ ህዝብ የዘላለም ባለውለታ ፓርቲ እንዲሆን አፋጣኝ ውሳኔ እንድሰጥ በጥብቅ እንጠይቃለን፡፡ ድል ለብልጽግና እና ለህዝባችን !!!

በድጋሚ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል ለህዝብ አንድነት ፀር የሆኑ ቡድኖች ተወግደው ለህዝብ ክብርና ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጡት የሚበዙበት የፍቅርና የሰላም እንዲሆን አጥብቀን እንሻለን።”

ያለልዩነት በአላማ አንድነት ብቻ ከተሰበሰቡ ህዝባዊ ለውጥ ኮሚቴ የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክ

ሚያዝያ 24/2016 ዓ.ም
ዎላይታ ሶዶ፤ ኢትዮጵያ Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *