ከየትኛውም አከባቢ በበጎ ፍቃደኝነት ስራና ሰራተኛ ለማገናኘት ካሉበት ሆነው የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ Admn መሆን ይፈልጋሉ❓

ማህበራዊ ሚዲያ በሁሉም ሰው ኪስ ውስጥ አብሮ በየትኛውም አከባቢ በቀላሉ ተደራሽ ሊሆን የሚችል ዘመናዊ መገናኛ ዘዴ በመሆኑ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ስራና ሰራተኛ ያለምንም ክፍያ በነፃ የማገናኘት ሀሳብ ያመነጨው ከሚዲያ አገልግሎት ባሻገር በተለይም ፍትሃዊ የማስታወቂያ ተደራሽነትንና አገልግሎትን በጥራትና በቀላሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም በየቦታው የሚስተዋለውን ከፍተኛ የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ረገድ የበኩሉን በጎ ሚና ለመጫወት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር የታለመ እንቅስቃሴ መሆኑን እንገልፃለን።

በዚህ በጎ ፍቃደኞች ካሉበት ሆነው በነፃ ያለምንም ክፍያ ስራንና ሰራተኛ ለማገናኘት በሚጀመረው ተግባር ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ተከታይ ባለው ፌስቡክ በተጫማሪ ሌሎች የሚዲያዎችን ኦፊሼል ዌብሳይት እና በቴሌግራም ቻናልም በተመሳሳይ መንገድና ጊዜ አገልግሎት እንደሚሰጥ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ከዚህ በፊት የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የተለያዩ የስራ ማስታወቂያዎች በተለይም የጨረታ ማስታወቂያዎች፣ የፍርድቤት ጥሪ ማስታውቂያዎች እና ሌሎች ማስታወቂያዎች በከተማዋ በተደራጀ ሁኔታ ባለመለጠፉና ተገቢ ጥበቃ ባለመደረጉ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ SNV ከተባለ አለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት ከ Mastercard Foundation ጋር በመተባበር የስራ ማስታውቂያ ቦርድ በዎላይታ ሶዶ ከተማ አማካይ በሆኑ ሶስት ቦታዎች ላይ አገልግሎት እንዲሰጥ በይፋ ማስጀመሩ ይታወሳል።

አሁን ደግሞ በዚሁ በቅርቡ በሚጀመረው በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና አፃፃፍ ላይ ልምድ ያላቸው በጎ ፍቃደኝነት ካሉበት ከየትኛው አከባቢ ሆነው የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ Admn መሆን የሚፈልጉ ግለሰቦች ዋና ተግባራቸው የሚላክላቸውን ወይንም የሚያገኙትን ስራ እና ሰራተኛ ለማገናኘት የሚያስፈልጉ መረጃዎችን በተመለከተ ብቻ በተጠቀሱ ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ለማሰራጨት የተፈቀደ ሲሆን በየትኛውም ሁኔታ ሌላ መረጃ ማስተላለፍ እንደማይፈቀድ መስማማት እንደሚገባ እየገለፅን ከታች በተጠቀሱ አድራሻችን ፍላጎታችሁን በማሳወቅ ፍትሃዊ የማስታወቂያ ተደራሽነትንና አገልግሎትን በጥራትና በቀላሉ ተግባራዊ በማድረግ በየቦታው የሚስተዋለውን ከፍተኛ ስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ የታለመውን በጎ ተግባር አካል እንድትሆኑ ከታላቅ አክብሮት ጋር ጥሪ እናቀርባለን።

ፍላጎታችሁን በአድራሻችን ይላኩ👇

👉 +254795315952 (WhatsApp Message only)
👉 info@wolaitatimes.com

ከዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ኤዲቶሪያል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *