ዶ/ር ገለታ ጴጥሮስ የተባለው ግለሰብ የቀድሞ የዎላይታ ዞን ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊየነበረው አቶ አሳምነው አይዛ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊነት በሚመሩበት ወቅት የመግደል ሙከራ ወንጀል የፈጸመውን የከፍተኛ እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሻሽሎ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የወሰነውን በይቅርታም በአመክሮም እንዳይፈታ አሁንም የዞኑ ፍትህ መምሪያ እየመሩ የሚገኙት አቶ እንዳሻው አባቴ የአመራር ትዕዛዝ በመቀበል በህገወጥ መንገድ መከልከሉን ከተበዳይ ባለቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የዶክተር ገለታ ጴጥሮስ ባለቤት ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያየዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 8/215 ዓ.ም 13 ዓመት ሲወስን ዐቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከሳሹ በወቅቱ የነበረውን ስልጣን ተጠቅሞ ጫና በማድረጉ የዞኑን ውሳኔ አሻሽሎ 15 ዓመት ከፍ አድርጎ የወሰነ ቢሆንም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሁለቱንም ፍርድ ቤት ውሳኔ አሻሽሎ በ 2 ዓመት እስራት እና ሁለት ሺ ብር መቀጮ እንዲቀጣ ቢወስንም በህጉ መሠረት የፍርድ ቤት ውሳኔና ትዕዛዝ ባለማክበር የማረሚያ ተቋም ኃላፊንና ቴኪኒክ ኮሚቴን በማስፈራራት በአመክሮም በይቅርታም እንዳይወጣ ተደርጎ እነሆ የሚፈታበት ጊዜ ካለፈ እነሆ ዓመት ሆኖታል” በማለት ቅሬታ አቅርባለች።

አንድ በዞኑ ፍትህ መምሪያ ላይ በዚህ የይቅርታ ምልመላ ኮሚቴ አባል የነበረውን ግለሰብ ስለሁኔታው ስንጠይቅ “የተፈጠረው እውነት እንደሆነና ባለፈው ዓመት ይቅርታ ምልመላ የቴኪኒክ ኮሚቴ መልምሎ ለዋናው ኮሚቴ አቅርቦ የፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ እንዳሻው የዋናው ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆኑ ከአቶ አሳምነው በተቀበለው ትዕዛዝ በህጉ መሠረት ቅጣቱን ጨርሶ መውጣት የነበረበትን ዶክተር ጴጥሮስ በቅም በቀልና ስልጣንን አለአግባብ በመጠቀም እንዳይወጣ ከልክሏል፥ የዘንድሮም ይቅርታ በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲከለከል ተደርጓል፥ ይሄን ጉዳይ ሁሉም ያውቀዋል” ሲል ገልጸዋል።

የዶክተር ባለቤት ደግሞ የነገሩ መነሻ ስትገልፅ ” ባለቤቴ የመግደል ሙከራ የፈጸመበት ምክንያት በሌ ሐዋሳ ከተማ ላይ የግል ኪሊኒክ ከፍተን እየሠራን የዞኑ ጤና ባለሙያ “ደረጃውን አታሟሉም ጉቦ ስጡን ካልሆነ አዘጋለሁ” ብሎ ያስፈራሯል፤ ከዛም ወደ መምሪያው ኃላፊና ሌሎች ጋር ቢመጣም ሚላሽ አላገኘም። ከዛን ቤቱ ተዘጋ። ባለቤቴ በተደጋጋሚ ተመላልሶ ረጅም ጊዜ ቢመጣም ምላሽ አላገኘም። ሁሉም ነገር የጨለመበት ዶክተሩ (ባለቤቴ) እኔ መጥቼ አቶ አሳምነውን እንዲለምን ጠየቀኝና ቢሮው መጥቼ የደረሰብን በደል ለምን ብዬ ስናገር የወከለውን ህዝብና የተቀመጠበትን ወንበር በማይመጥን መንገድ ከእርሱ ጋር እንድተኛና ወሲብ እንዲፈፅም ጠየቀኝ፣ ይሄን ሁሉ ጫና በባለቤቴ ላይ ለምን እያደረሰ እንደሆነ ስለገባኝ በጣም ደነገጥኩኝ፥ ለባለቤቴ ነገርኩት፣ በዛ ተናድዶ እስከቢሮ ድረስ መጣ፥ ፍላጎቴ በህጋዊ መንገድ ለመጠየቅ ነበር ግን አልተቻለም። አሁን ግን በህጉ መሠረት ባለቤቴ ቅጣት ጨርሶ በአመራር ትዕዛዝ ብቻ በዎላይታ ሶዶ ማረሚያ ተቋም ውስጥ ይገኛልና ህግ ይዳኘን” በሚል ለሚመለከተው አካል ጥሪ አቅርባለች።

በዎላይታ የተደቀነው የፍትህ ዕጦት መፍትሔ የሚያገኘው መቼ ነው ? ፍትህ ለምን በገንዘብ ይሸጣል ❓ለምንስ በአመራር እጅ ወደቀ❓

በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *