በዎላይታ ዞን የሶስት ወር ደመዝ ያልተከፋላቸው የመንግስት ሰራተኞች ሰልፍ ወጡ

በዎላይታ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ባለፈው ሳምንት ገልፆ ነበር።

በዛሬው ዕለት የሶስት ወር ደሞዝ ባለመክፈሉ አደጋ ላይ ወድቀናል የሚሉ የዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ መንግስት ሰራተኞች በሰላማዊ ሰልፍ እስከ ክልሉ ርዕሰ መስተደድር ቢሮ ድረስ መሄዳቸው ተሰምቷል።

የመንግስት ሰራተኞችን የወከሉ ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸውን ይዘው ወደ አደባባይ እንዲወጡ ያስገደዳቸው የወረዳውን ሆነ የዞኑን መንግስት በተደጋጋሚ ቢጠይቁም በቂ ምላሽ ባለመሰጠቱ እንደሆነ አንድ የሰልፉ አስተባባሪ ገልፆልናል።

በተቃራኒው ዞኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ከ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ የተገለፀ ቢሆንም በአከባቢው ልማት ስራዎች ቆሞ በአብዛኛው መዋቅር ደመወዝ መክፈል አለመቻሉ ለበርካቶች ጥያቄ ፈጥሯል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *