ያለልዩነት በአላማ አንድነት ከተሰበሰቡ ህዝባዊ ለውጥ ኮሚቴ ለኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት

ሰሞኑን የሌብነት ሰንሰለት እና ኔትወርክ ምርመራ በተመለከተ አመራሮች ያደረጉት “እርቅና ድርድር” የግላቸው እንጂ የዎላይታን ህዝብ የማይመለከት ብሎም አብሮ ተባብሮ ለመሥረቅ ያደረጉት አዲሱ የሌብነት ሰንሰለት ዝርጋታ መሆኑ መታወቅ እንዳለበት እናሳስባለን።

የዎላይታን ህዝብ ለመጨቆንና ለመጉዳት በቅርቡ በዎላይታ ውስጥ በተፈጠረው በአበልጅ፣ በጎሳ፣ በጎጥ እና በኃይማኖት በመደራጀት የዎላይታ ህዝብ ችግር ውስጥ እንዲገባ ያደረጉ አመራሮችን ( በተላይም አቶ ተስፋዬ ይገዙ እና ጀሌዎቹ የሚመሩት ) ህገወጥ ቡድን ከዎላይታ አብራክ ወጥተው የዎላይታ ህዝብን በመዝረፍ፣ በመስረቅ እና በዎላይታ ህዝብ ላይ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳት እያደረሰ መቆየቱ ይታወቃል።

በዚህም የዎላይታ ህዝብ አምርሮ ታግሎ መስመር ለማስያዝ ትግል በሚያደርግበት በዚህ ጊዜ አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው የብልጽግና መር መንግሥት እና ፓርቲ ለዎላይታ ህዝብ ያለውን ንቀትና ጥላቻ በሚያሳይ መልኩ በመንግስት ተዋቅሮ በህዝብ ድጋፍ በተደረገ ምርመራ የተረጋገጠውን ሌብነታቸውን እና የሌብነት ሰንሰለቱን ችላ በማለት በቡድኑ አውራው በአቶ ተስፋዬ ይገዙ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጣለውን እገዳ ማንሳቱ የብልጽግና ፓርቲ ለዎላይታ ህዝብ ክብር እንደሌለው ብሎም ንቀትና ጥላቻ ያለው በመሆኑ ይህንን ውሳኔ በፅኑ እንቃወማለን::

ኢትዮጵያን የመሰለ ትልቅ አገር የሚመራ ብልጽግና ፓርቲ በከፍተኛ ዲስፕሊን እና ቆራጥነት ይንቀሳቀሳል ተብሎ በሚጠበቅበት በዚህ ሁኔታ የብልፅግና ፓርቲ የአንድ ሥራ አስፈፃሚ አባል ሌብነትን ለመሸፋፈን የሚያደርገው ጥረት የሚመስል ነገር የሚቀጥል ከሆነ የዎላይታ ህዝብ ይህን አቶ ተስፋዬ ይገዙ የሚመራውን ቡድን በነፍሱ ተወራርዶም ቢሆን ለማስታገሰ ብሎም ለማስወገድ የትኛውንም መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን እንገልፃለን።

በምርመራ የተረጋገጠው አቶ ተስፋዬ ይገዙ የሚመራው ቡድን በዎላይታ ህዝብ ላይ ያደረሰው ሌብነት፣ የስርቆት ጉዳት የህግ ተጠያቂነት የማይሰፍን ከሆነና ሌቦች በሹመት የሚቀጥሉ ሆኖ በህዝቡ ላይ የሚደርስ በደል የሚቀጥል ከሆነ የዎላይታ ህዝብ መንግሥትን ሳይጠብቅ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ ከወዲሁ እናረጋግጣለን።

ሰሞኑን በተደረገው የሌብነት ሰንሰለት እና ኔትወርክ ምርመራ በተመለከተ ክልል ያሉ የመንግሥት ሹማምንት ያደረጉት እርቅና ሠላም የግላቸው እንጂ የዎላይታን ህዝብ የማይመለከት ብሎም አብሮ ተባብሮ ለመሥረቅ ያደረጉት አዲሱ የሌብነት ሰንሰለት ዝርጋታ መሆኑ የሚታወቅ ስለሆነ በዚህ ምክንያት የሚፈጠር ችግር ካለ የፌደራል መንግሥት እና የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊነት እንደሚወሰድ ካሁኑ እንዲታወቅ እናሳስባለን::

የዎላይታ ህዝብ አንድነት ጠላት የሆኑት የአበልጅ አደረጃጀት መሪ እና አባላት ከህዝባችን ተወግዶ ማየት የመላው የዎላይታ ህዝብ ከፍተኛ ፍላጎት ስሆን ብልጽግናም ይህን ክፉ አመኬላ ከህዝባችንና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማስወገድ አማራጭ የሌለው መሆኑን ተረድቶ ተግባራዊ የሚያደርግ ከሆነ ብልጽግና ለዎላይታ ህዝብ የሁልጊዜ ወይም የዘላለም ባለውለታ እና የልብ ፓርቲ መሆኑን ሊናረጋግጥ እንፈልጋለን::

እነዚህ የመሬት ሌቦች በስማቸው ሳይሆን በፈጠሩት የጥቅም ኔትዎርክ የሰረቁትን ሀብትና ንብረት በህጋዊ መንገድ ልነጠቁ ይገባል፡፡ የተሰረቁ ሀብቶችም ለዎላይታ ህዝብ ገቢ ተደርጎ አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ እናሳስባለን።”

ያለልዩነት በአላማ አንድነት ከተሰበሰቡ ህዝባዊ ለውጥ ኮሚቴ የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት

ዎላይታ ሶዶ፣ ኢትዮጵያ
ግንቦት 9/2016 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *